እናትነትሽን

217

እናትነትሽን ልባችን ተቀብሏል
ትህትናሽንም ውስጣችን አድንቆታል
መከታ ነሽ እንቺ ለኛ ለልጆችሽ
ይዘረጋል ሁሌ ንፁህን እጆችሽ /2/

ማርያም ሆይ አንቺ ለኛ ረዳታችን

መሸሽጊያ ጉያ ንፁህ እናታችን
ወዳንቺ ስንሮጥ ስንማፀንሽ
ምን ግዜም ይራራል ትሁቱ ልብሽ /2/

ስለኛ ለምኚ ስለበደላችን
አማልጅን ከልጅሽ ስርየት እንዲሰጠን
ልመናችንን ወዳንቺ አድርሰናል
አናፍርም ከእንግዲህ ባንቺ ተማምነናል /2/

እናታችን ኣንቺ ድንግል ማርያም ነሽ
ሁሌ ይጣፍጣል ስንጠራው ስምሽን
አንቺን እናመስግን እንታመንሽ
ምን ጊዜም አይለየን ምርኩዝ ድጋፍሽ /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top