ብፅእት ነሽ አንቺ የጌታዬ እንባ… አሀሀ
ፀጋን የተሞላሽ የፍጥረት እመቤት…አሀሀ
የፅዮን ደጃፍ ነሽ የሰላምም ንግሰት..አሀሀ
ኦ ማርያም… አሀሀ ማርያም…አሀሀ
ማርየም…አሀሀ
እስከ አለም ዳርቻ ሁሉን የፈለገ
ከትውልድ መካከል አንቺን የመረጠ
ከብሮ ያከበረሽ ሁሉን የፈጠረ
እግዘአብሔር አብ ኣንቺን የወደደ
አንድያ ውድ ልጁን ወደ አንቺ ላከ
የእግዚአብሔር ቃል ከአባቱ ሳይለይ
ከአንቺ ተፀነሰ ፍፁም ሳይወሰን
የማይመረመር የማይመጠነው
የመለኮት እሳት በማህፀንሽ ያደረው
እረቂቁ ሚስጠር በመስቀል ያየነው
አንቺን የወደደ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው
ማህፀንሽ ያደረ ወልድ ዋህድ ቅዱስ ነው
ያፀናሽም እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው
ይህ ነገር ምንኛ እፁብ ድንቅ እኮ ነው
ይሄ ሁሉ ሚስጥር ከአይምሮ በላይ ነው
አንቺ እኮ ልዩ ነሽ የነቢያት ትንቢት
የሐዋርያት ሞገስ የሰማእታት እናት
የፍጥረት እመቤት የመላእክት እህት
የተፀነስሽ ነሽ ያለአዳም ሐጥያት
ትውልድም በፍቅር የሚልሽ ብፅእት
