አዝ. ኦ መስቀል ሆይ መዳኛችን
ኦ መስቀል ሆይ ቤዛችን
ኦ መስቀል ሆይ መድኃኒታችን
ብርሃንህን አብራልን
1. ኢየሱስ ባንተ ተሰቅሎ ነው
እኔን ከኃጢአቴ የፈወሰው
ራሱን ለሥቃይ የዳረገው
ከዚያም አልፎ የሞተው
አዝ. ኦ መስቀል ሆይ መዳኛችን
ኦ መስቀል ሆይ ቤዛችን
ኦ መስቀል ሆይ መድኃኒታችን
ብርሃንህን አብራልን
2. ኦ መድኃኒያለም ክርስቶስ
እኔም መስቀልህን ልዳስስ
ወደርሱ ዘንድ ልገስግስ
ከበበደሌም እንድፈወስ
አዝ. ኦ መስቀል ሆይ መዳኛችን
ኦ መስቀል ሆይ ቤዛችን
ኦ መስቀል ሆይ መድኃኒታችን
ብርሃንህን አብራልን
3. ድኜ ከችግር ከሕመሜ
ከመስቀልህ ሥር እኔ ቆሜ
ከፀጋህ እንዳገኝ ተሳልሜ
ታየኝ በክርስቶስ ተሸልሜ
አዝ. ኦ መስቀል ሆይ መዳኛችን
ኦ መስቀል ሆይ ቤዛችን
ኦ መስቀል ሆይ መድኃኒታችን
ብርሃንህን አብራልን
4. መስቀልህን ይዤ ልንገላታ
እንዳንተ ልሁን የኔ ጌታ
ለሰይጣን ፈጽሞ ላልረታ
ቆርጫለሁ ሳላመነታ
አዝ. ኦ መስቀል ሆይ መዳኛችን
ኦ መስቀል ሆይ ቤዛችን
ኦ መስቀል ሆይ መድኃኒታችን
ብርሃንህን አብራልን
5. በእንባ ባሕር ውስጥ የነበረች
በጭንቀት ሙላት የተዋጠች
ሥቃይዋን በእምነት ድል ያረገች
በመጽናቷ ልዕልት ሆነች
አዝ. ኦ መስቀል ሆይ መዳኛችን
ኦ መስቀል ሆይ ቤዛችን
ኦ መስቀል ሆይ መድኃኒታችን
ብርሃንህን አብራልን
