አመስግኚው ነፍሴ ሆይ ተነሺ በዝማሬ
በዝማሬ እግዚአብሔርን ባርኪ
ነፍሴ ሆይ ስራውን ተርኪ
1. ከአፈር ከትቤያ ከውድቀት ያነሳሽ/2/ ነፍሴ ሆይ ተነሺ
የዛሬው አይደለም ያንቺ ማንነትሽ ስዕልሽ የጥንቱን አስቢ
ምስጋናን ዘምሪ ቅኔንም ደርድሪ/2/ ወጥተሽ አደባባይ
ንጉስ ለወደደው እንዲህ ተደረገ ተሰራ ብለሽ ለሰው አሳይ
አመስግኚው ነፍሴ ሆይ ተነሺ በዝማሬ
በዝማሬ እግዚአብሔርን ባርኪ
ነፍሴ ሆይ ስራውን ተርኪ
2. እንደ ኃጢያትሽ ዋጋን አልከፈለሽ አልጣለሽ ጨክኖ አልሰበረሽ
ሃይሉን እንደሚያድስ እንደብርቱ ንስር አረገሽ በምህረቱ ምሮሽ
ፍቅሩ ገኖልሻል ለምስጋና ቁሚ ተነሺ መዝሙርን ዘምሪ
ቸርነት ማዳኑን ለሰው ልጆች አውሪ ንገሪ በይ ተነሽ አብስሪ
አመስግኚው ነፍሴ ሆይ ተነሺ በዝማሬ
በዝማሬ እግዚአብሔርን ባርኪ
ነፍሴ ሆይ ስራውን ተርኪ
3. ውብ አርጎ አሳምሮ በፊቱ ያቆመሽ/2/ አይደለም በስራሽ
እንዲያው በፀጋው ነው እግ/ር የረዳሽ ያገዘሽ ይህን ቀን ያሳየሽ
በገናን ደርድሪ ክራርን ከርክሪ/2/ ለባለውለታሽ
ምስክር ሁኚለት ምስጋናሽም ይመር አይነስ ላኮራሽ አምላክሽ
አመስግኚው ነፍሴ ሆይ ተነሺ በዝማሬ
በዝማሬ እግዚአብሔርን ባርኪ
ነፍሴ ሆይ ስራውን ተርኪ
