እግዚአብሔር ንገስ ባምልኮ
ሁሉን ቻይ ንጉስ ነህ እኮ
እኔም ልዘምር ሰሆታ
ባልከፍልም ያንተን ውለታ
ንገስ በኔ ላይ ክብርህ በኔ ላይ ይታይ
ክበር በኔ ላይ መንፈስህ ይውረድ ይንካኝ
ቅኔ ቢደረደር ቃላትም ቢቀመር
ለመንግስትህ ስፋት አልተገኘም ወደር
በሰማይ በምድር አምሳያ የለህም
አልረካሁም እኔ ብዘምርልህም
የህይወቴ ምሰሶ የመኖሬ ሚስጥር
ፍቅርህን አስካውቀው አልገባኝም ነበር
ዛሬ ተረድቼ ያንተን ክብር ላውራ
አንተን ብቻ አድርጌ የህይወት አባወራ
ማን ልበልህ ጌታ እኔ ቃላት አጣሁ
ካንደበት የሚፈልቅ ላንተ ደስ የሚሰኝ
መንፈስህ ያበርታኝ አንተን ላክብርበት
የምስጋና ዜማ ባፌ ላውጅበት
