ታሪክ ሲመረመር መዝገቡ ሲገለት
አንድ እንኳ አይገኝም እግዚአብሄርን የሚበልጥ /2/
በዘመናት ሁሉ ያልታየለት አቻ
የዘላለም አምላክ እግዚአብሄር ብቻ
እግዚአብሔር ሲመጣ ማን ፊቱ ይቆማል /2/
ትልቁ ተራራ ፊቱ ይፈራርሳል /2/
ምድረበዳው ይናወታል ጫካው ሁሉ ይገለጣል
በእግዚአብሔር ፊት ማን ይቆማል
አለቱ ይሰነጣጠቃል የተሰወረውም ይወጣል
በእግዚአብሔር ፊት ማን ይቆማል /2/
መኖሪያው ሠማያት ማደሪያው ነው ልዩ
ባይምሮ አይታሰብ ጌታዬ አኗኗሩ
ከመረዳት በላይ ብዙ ከፍ ያለ ነው
ዘመኑ ፍጻሜ ማለቂያ የሌለው
ዘማሪው ቢዘምርቅኔን ቢያወጣ
ሠባኪው ቢተርክ መገለጥ ቢያመጣ
ሰው ይሞታል እንጂ ስለርሡ እያወራ
ቢነገር አያልቅም የእግዚአብሄር ስራ
