ትህትናን ፍቅርን ተላብሰሽ
በጸጋው ጸጋን ተጎናጽፈሽ
ውብ እናት ማሪያም ተገኘሽ
ያቺ ቀን እረ እንዴት ውብ ናት
ፍቃድህ ይሁን ያልሽበት
የሰው ዘር ከሞት የዳነበት
ጨለማ ስፍራ የለቀቀበት
ነሽ አንቺ ባለውለታችን
የመዳን መንገድ ምክንያታችን
ምንኛአንቺ እድለኛ ነሽ
እግዚአብሔር በፍቅር የመረጠሽ
በማህፀንሽ ክርስቶስ አደረ
የዓለም ተስፋው ለመለመ
የወጣው ከኣንቺ ማህፀንማ
ገፈፈው የምድርን ጨለማ /2/
ከሴቶች ሁሉ የተለየሽ
እግዚአብሔር ወዶ የመረጠሽ
የሚስጥሩ ተካፋይ ሆነሻል
በመንፈስ በዕምለት ፀንተሸል
እሽታሽ ለዉጥ ሆነ ለአለም
የሞት ሀይል ጠፋ ለዘላለም
