የንተን መልካምነት በአእምሮዬ
አስቤ አልጨርሰው ተናግሬ
እንዲያው ዝምብዬ እኖራለሁ
በህይወት ዘመኔ እገረማለሁ
ሁሌም/3/ እገረማለሁ – ያረክልኝን እያየሁ
ሁሌም/ እደነቃለሁ – ውለታህን ስላየሁ
ከየት ልጀምር አንድ ሁለት ብዬ
የውለታው ዝርዝር ይሄ ነው ብዬ
ቃላት አይበቃኝ ዓረፍተ ነገር
እንዲህ ነው ብዬ እንዳልናገር
ግርምት ብቻ ነው ህይወቴን የሞላው
ምን አለኝ ብዬ እንዲህ ነህ የምለው
ሁሉም ይስማማል በአንድ ነገር
አንተ መልካም ነህ ጌታ እግዚአብሔር
ለእኔስ ልዩነህ ከዚያም በላይ
ያረክልኝን ውለታህን ሳይ
ተመስገንልኝ የልቤ ጌታ
ምላሽ የለኝም ላንተስ ውለታ
ለምን ወደድከኝ ብዬ ሣስበው
ምክኒያት የለህም ኧረ እንዲሁ ነው
ጥልቅ ነው ፍቅርህ ያንተ ደግነት
ፍፁም የጠራ የሌለው እንከን
የማያቋርጥ መልካም ደግነት
ካንተ ይፈሳል የፍቅር ጅረት
