ፍቅር ቢሆን ነው

236

ታሪኩ የሚገርም አንድ ሰው አውቃለሁ

እጅግ የተናቀ ደም ግባት የሌለው
አትኩሬ እንዳላየው ፈቴን ሰወርኩበት
እርሱ ግን ለኔ ሲል ተነዳ ወደ ሞት

በደሌን ሊሸከም ቁስሉ ፈውስ ሊሆነኝ
ያ ሚስኪን እየሱስ ለኔ የሞተልኝ
እንዲህ መዋረዱ ለኔ መቸገሩ
ከቶ ያላወቅሁት ምንድነው ሚስጥሩ

እጅግ ረቂቅ የሰው እውቀት የማይፈታው
ያን ድንቅ ተአምር የተሠራው
ላውቀው እፈልጋለሁ ሚስጥሩ ምንድን ነው
በሕይወቴ እንዳልረሳው

ፍቅር ቢሆን ነው ነው ነው
ስለኔ ሲል ያወረደው /2/

ሕይወት ሊሆነኝ የሱ ስቃይ ለኔ
ባርኮት እንዲሞላው የስደት ዘመኔን
ሰው ሊያደርገኝ ወዶ ሞትን የመረጠው
ትርጉሙ የጠለቀ አንድ ምስጢር አለው

ሊታረድ ሲነዳ ዝም እንደሚል ጠቦት
ምን አስገድዶት ነው ስለኔ የሚሞት
ውለታ እንዳልለው አስቀድሜ አላውቀው
ይህ ሰው ስለኔ ሲል ለምንድነው የሞተው

በደሙ ከሰይጣን እጅ ያደነኝ
በሞቱ ከሞት ግዛት ያወጣኝ
በኔ ላይ ምን አየ ወደኔ ምን ሳበው
ኃጢያቴን ይቅር ያለው

ፍቅር ቢሆን….
በጥፋት ጐዳና በመቅበዝበዝ ስኖር

እሱ ነው ያዳነኝ ከመከራ ከጣር
እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን የፈጠረ
በደሌን በሙሉ በሱ ላይ አኖረ

ነፍሱን ለኔ ሊሰጥ ፈቃዱ የሆነው
አምላኬ በኔ ላይ አላማው ምንድን ነው
እያልኩ ሳጠያይቅ መልሱን እስካገኘው
አልገባኝም ነበር ለኔ የፈጸመው

ኃይል ክብር በሉ ዘንድ ሞልቶ ያለ
ሞት ጣር ስቃይን ተቀበለ
ዛሬ ግን ሲገባኝ ምስጢሩን ስረዳው

ይህንን ያደረገው
ፍቅር ቢሆን …….

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top