ድካም ይገባሃል አንተ አትሰለችም/2/
ወደጅም ዘመድ ሲርቅ አንተግን አትሸሽም/2/
ማረፊያዬ /3/ ነህ የዘላለሜ/2/
1. እንዳንተ አላየሁም የውስጥ የሚረዳ
የድሃ አደግ አባት ደራሽ ለተጎዳ
እኔ አውቅሃለሁ ከማንም በላይ
በመልካምነትህ የሌለህ መሳይ/2/
ድካም ይገባሃል አንተ አትሰለችም/2/
ወደጅም ዘመድ ሲርቅ አንተግን አትሸሽም/2/
ማረፊያዬ /3/ ነህ የዘላለሜ/2/
2. ሃጢያት በደሌን ከኔ አላሸሸህ
በፍቅር ቀረብከኝ ይልቅ ለኔ ራርተህ
ከባርነት ቀንበር ነፃ አወጣኽኝ
ሞት የሚገባኝን በህይወት አኖርከኝ/2/
ድካም ይገባሃል አንተ አትሰለችም/2/
ወደጅም ዘመድ ሲርቅ አንተግን አትሸሽም/2/
ማረፊያዬ /3/ ነህ የዘላለሜ/2/
3. አንዲት የሚቆጠር በጎነት ሳይኖረኝ
ከነቆሻሻዬ በጉያህ አቀፍከኝ
ምንኛ ልዩ ነው የሱሴ ፍቅርህ
የምትወድበት ምክንያት የሌለህ/2/
ድካም ይገባሃል አንተ አትሰለችም/2/
ወደጅም ዘመድ ሲርቅ አንተግን አትሸሽም/2/
ማረፊያዬ /3/ ነህ የዘላለሜ/2/
