እንዴት ያስችለኛል ዝም ልበልስ ብል
ፍቅርህ ልቤ ገብቶ ሕይወቴን ቀይሯል / ለውጧል /2/
ከስምህ በቅተቀር እኔ አላውቅህም
ከዝናህ በስተቀር እኔ አላየሁም
ዛሬ በህይወቴ ገብተህ ስትሰራ
አይቼ ተነሣው ስላንተ ላወራ
በሄድኩበት ሁሉ ስላንተ ልመስክር
ስላደረክልኝ ድንቅና ተአምር
ስላንተ እያወራሁ በዘመኔ ሁሉ
አሣልፈዋለሁ እድሜዬን በሙሉ
ዝም ልበልስ ብል እኔ አይቻለኝም
ፍቅሩ ልቤ ገብቷል ልጠላው አልችልም
ሀብት ወርቅና ብር እኔን አታጓጉም
እናተ ቅሩ እንጂ አባቴን አልተውም
በዜማ ላወድስ ላንተ ልዘምር
በሄድኩበት ሁሉ ስላንተ ልመስክር
