ይብዛልህ ክብር የብዛልህ መደነቅ
ተባረክ የኔ ጌታ /2/
ጉዳይ አለህ ከታናናሾችህ ጋር
ነገር አለህ ዛሬም ከእኔ ጋር
አሰራርህ ከማንም ልዮ ነው
ለዘላለም የሚመስልህ የለም
ተባረክ የኔ ጌታ/2/
ምን ቢከፋ ቢርቅህ ቢጠፋ
ሰው ፍጡርህ በደሉ ቢሰፋ
አባትነትህ ወጣ ለፍለጋ
መጨረሻው ባንተ እንዲረጋ
ተባረክ የኔ ጌታ/2/
የዕድቅን ፀሐይ አብርተህልኛለል
ፊትህን ወደ እኔ መልሰህልኛል
አቤቱ አስተያየትህን
ለኔ አጠንክረሃል /4/
ትራራለህ ዛሬም ትራራለህ
ትሳሳለህ ዛሬም ትሳሳለህ
ታነሳለህ መቼ አንተ ታልፋለህ
ነፃነቴን አውጀህልኛል
ለነብሴ መራራትህን
ጌታ ለኔ አብዝተሃል /4/
ትነካለህ ፈውስም ትሆናለህ
መዳን ሊሆን ነፍስን ትሰጣለህ
ያደፈን ማንፃትን ታውቃለህ
አትጠየፍ ሁሉንም ታቅፋለህ
