እግዘአብሔር ሆይ በዙፋንህ ላይ
ከብረህና ደምቀህ ተውበህ ትታይ
በእኔ ትሰራለህ በአንተው አገልጋይ /2/
ዙፋንህ ይስፋ የኔ ጌታ
አምልኮም ይሁን ለውለታህ /2/
ያልከው ሁሉ ሲሆን ድንቅ ስራ
ፍጥረት ይደነቅ እንደገና
መላእክት ቅዱሳን ዙፋንህን ከበው
ቅዱስ ቅዱስ ይላሉ ማደሪያህን ሞልተው
እኔም አገልጋይህ ከበታች ቆሚያለሁ
በከበሮ እንቢልታ አዜምልሃለሁ
በዙፋንህ ያለህ የማትሻር አባት
የነበርክ ያለህ ከዘመናት በፊት
የሰማይ ቅዱሳን ፅድቅህን ያወራሉ
ህዝቦች በሙሉ ክብርህን ያያሉ
ክብርህና ዝናህ የገነነ አባት
የምስኪኑ ወዳጅ የደካማው ረዳት
ሰዎች ላይጠፉ ሊኖራቸው ህይወት
በኢየሱስ ገለጥክ ፍቅርህንና ምህረት
አመልካለሁ ኢየሱሴ
ላመስግንህ በውዳሴ
ዘውትር ላምልክህ በምስጋና
አምላክ እንዳንተ የለምና
