እንካችሁ ብሉ ይኸው ስጋዬን
እንካችሁ ጠጡ ይኸው ደሜን
ለዘለዓለም ሰላም ይሰጣል
ለህይወት ዕረፍት ፅድቅን ያመጣል /2/
ለኃጥያት ይቅርታ ለብዙ ሰው
የአዲስ ኪዳን ደሜ የሚፈሰው
ብሎ ተናግሯል ለሁላችን
ራሱን የሰጠን መድኃኒታችን
ስለብዙዎች የሚሰጠው
ይኸው ለእናንተ ስጋዬ ነው
እንካችሁ ደሜን ተካፈሉት
ስለሚሰጣችሁ የዘለዓለም ህይወት
በአባቴ መንግስት አዲሱን ፅዋ
እስከምጠጣ ከእናንተ ጋራ
የወይን ጭማቂ ከዚህ በኋላ
እስከዚያች እለት አልጠጣም ሌላ
