ከነገስታት በላይ ንጉሥ አንተ ብቻ
የሚወዳደርህ አልተገኘም አቻ
ከቶ አይናወጥም ያንተ መቅደስህ
ቅዱስ ቅዱስ እያልን እንዘምርልህ
እንዘምርልህ /8/
ለታመኑብህ ፅኑ ኃያል መከታ
የሠረገላን ጦር በክንድህ ምትረታ
ቃልህ ተፈፅሞ ሲተረክ ስንሰማው
መንፈስህ ሞልቶብን ንገሥ እንልሃለን
ንገስልን /8/
አዕላፍ ቅዱሳን የሚሰግዱልህ
ትውልድ ሁሉ ዛሬ የሚመካብህ
ሲለወጥ አላየን ቃልህ ያንተ ጌታ
እናከብርሃለን ክበር የኛ ጌታ
ክበርልን /8/
ከማንም በላይ ነህ በዙፋን በግርማ
ሚረታህ አላየን ጆሮአችን አልሰማ
የታሰረውን ነፃ ታወጣለህ
ኧረ ጌታችን ሆይ እንስገድልህ
እንስገድልህ /2/ ስለሚገባህ ምስጋና ክብር
ተመስገንልን /2/ ለአምላክነትህ ተመስገንልን
ተባረክልን /2/ ከምንም በላይ ከፍ በልልን
ተወደስልን /2/ አምላካችን ነህ ተወደስልን
