አንተ ለእኛ

245

አንተ ለእኛ ስጋህን ሰጥተህ
አንተ ለእኛ ደምህን አፍስሰህ
እንኖራለን ዛሬም ፀጋህ በዝቶልን
እንኖራለን በአንተን ተደግፈን /2/

ቅዱሱ ስጋህ ህይወት ይሰጣል
ደምህን የጠጣ በአንተ ይኖራል
ምስጢሩ ይህ ነው ጌታ ያንተ እኮ
ላመነ ሁሉ በአንተ ተልዕኮ /2/

የዘላለሙን ስጋዬን ብሉት
ይህንን ደግሞ ደሜ ነው ጠጡት
ተቀበሉና ከርሱ ውሰዱ
ይኸውላችሁ የጌታ ማዕዱ /2/

ብለሃልና አለኝ ህይወት
ኢየሱስ አንተ ነህ እውነት
ሁሉም ይሆናል ይፈፀማል
ስጋህን የበላ በህይወት ይኖራል /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top