መልካሙ ወዳጄ ከጉያህ ሸሽገኝ
አቅም አጣሁ ደከምኩ ብሶቴ በዛብኝ
ማረፊያ አጥቼ እንዲያው ስንከራተት
ደራሹ ኢየሱስ አድነኝ ከጥፋት
የውስጥ ሚስጥሬን እስኪ ላጫውትህ
እርዳኝ የእኔ ጌታ ከጎኔ ሆነህ
በእልፍኝ ውስጥ ሆኜ አንተን ላምልክህ
ሁሉን ነገር ትቼ አንተን ልከተልህ
አቅልልልኝ ጌታ የውስጤን ሸክም
በርትቼ እንዳልፈው ይህንን ዓለም
በኃጥያቴ ብዛት ጨንቆኝ ደክሚያለው
ጌታ ሆይ ከቤትህ ዛሬ መጥቻለው
ጎዶሎ ህይወትን መሙላት የሚችል
ከኢየሱስ በቀር ኧረ ማንን ልበል
ተጎድቻለሁኝ ከአንተ በመራቄ
ከእንግዲህ በቅቶኛል ዓለማዊነቴ
