መንገደኛነቴ ጥልቅ ሚስጥር አለው
ብዙ የሚያናግር ጉዞውም ረጅም ነው
ጌታ ሲጠይቀኝ ምንድነው በማለት
ቆም ብዬ መለስኩኝ በአዘነ አንደበት
ዕድሉን አግኝቼ ሁሉን ሳወራልህ
ያልተገነዘብኩህ ለካ ወዳጄ ነህ
ስትቀሰቅሰኝ አስተዋይ እንድሆን
ቅዱሳት መፃህፍትያስገነዘቡትን
ከጎኔ እየተጓዝክ ጉዳዩን ስትነግረኝ
ልቤ ይቃጠል ነበር አንተ በምትለኝ፤ በምትነግረኝ
የማይረሳ ሆኖ ሁሉ የገጠመኝ
ከእኔ ጋር ተጉዞ አይቻለሁ ቀርቦኝ
እመሰክራለሁ እንዴት እንዳገዘኝ፣ እንደረዳኝ
ተመቸው ወዳጄ የመንገዱ ርዝመት
የፀሀይ መጥለቅ የጊዜውም መምሸት
ማደርን እሺ አለ በቤቴም ገባልኝ
እንድገነዘበው እንጀራን ሊሰጠኝ፣ ሊመግበኝ
በመንገዴ ታሪክ ጌታ ሲገናኘኝ
ያንተ ወዳጅነት ምንም አያሳቅቅ
ገበናዬን ብታይ ከቶ የማትንቅ
ጌታ አቀራረብህ ስላበረታታኝ
ልቤን ልክፈትልህ ሁሉንም እንድታይ፤ እንድታቃኝ
