አዳም የት ነህ ያለኸው ብለህ ጠይቀህ
ለእኔ ተቆርቁረህ መች ጠፍቼብህ ቦታዬን ዘንግተህ እዚህ አለሁ
የሚል መልስ ሆኖ ናፍቆትህ
በአትክልቱ ቦታ እሴራን ሸሸግሁና
የተሻለ አድራሻ መስሎኝ ታየኝና
እቁትነቴን ሳላፍርበት ድሮ
አሁን ዘገነነኝ መጣብኝ አምርሮ
ቀረብ ብዬ ሳየው የሞላው ልቤን
አንዱ የሚያስጨንቅ የሚጎዳ እራስን
ሌላው የሚያፅናና የሚሆን ለብርታት
በል እዚህ አለሁኝ አንተ ውድ አባት
ድምፅህ ካለሁበት ስልል ብሎ ቀርቦኝ
አንተን ሸሽቶ መሄድ እንዴትስ ሊቻላኝ
የት ያለኸው የሚለው ጥያቄህ
ውስጤን ከነከንኝ እዚህ አለሁ እንድል
የት እንዳለሁኝ ሳይ የውስጥ መንፈሴን
ብዙ ድርቀት ያለው የተጠማውን
የሚብለጨለጨውን ልቤ ከሚመኝ
አንተው አረስርሰው እርካታ እንዳገኝ
