ዝምታዬን

252

ዝምታዬን / ጽሞናዬን ጌታ ፈለከው / ወደድከው
ቃልህን የሚሰማ ሆኖ አገኘኸው

ውስጤን የሚረብሽ ሰላም የሚነሳኝ

በፊቴ የሚነበብ ብዙ እንዳስጨነቀኝ
ማርታ ማርታ ብለህ ይህንን ታዝበህ
ዝምታን / ጽሞናን ጠቆምከኝ አንድ እርሱ ነው ብለህ

የልብ ወዳጅ መጣህ ልትጎበኘኝ
ጊዜህን ሰጥተኸኝ እንዴት ነህ ልትለኝ
ከጭንቀቴ በቀር እኔን ባታገኘኝ
ዝምታን / ጽሞናን ሰጥተኸኝ ወደአንተ አቀረብከኝ

ለካ የቀረብከኝ የሚታይህ ፊቴ
ሸክም አልባ ሳይሆን ነው ከነቀንበሬ
በዚህ ሁሉ ውጥረት እንዳውቅ መኖርህን
ዝምታን/ጽሞናን አሳየኝ ሚሞላ የልብን

ማንም የማይወስደው ከልብ የሚቀረውን
መምረጥን አሳየኝ ያ የተሻለውን
ተመስጬ እንድኖር በማሰብ አንተን
ዝምታን / ጽሞናን ሸልመኝ የሚሆነኝ ፍቱን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top