ባለህ ሙሉ ግርማ

255

ባለህ ሙሉ ግርማ ባለህ ክብርህ ልክ /2/

በልቤ ዙፋን ላይ ትመለካለህ ከልካይ የለህ
እንዲያው በሆነልኝ እራሴን ሰጥቼ እራሴን ሰውቼ
ደስ ባሰኘሁህ ክብሬን ሁሉ ትቼ ተሰጥቼ

ማለዳ ስነሳ አልፎ ጨለማዬ
ምስጋናህ ባፌ ነው አልዋሽም ጌታዬ
ሲያመልኩህ ይረፉ ስጋዬ ና ነፍሴ
ዛሬም እንዲህ ብለው ተመስገን ኢየሱሴ

በቦታ አትወሰን አለህ ሁሉም ቦታ
እግዚአብሔር አዋቂ ሀያል ሩህሩህ ጌታ
በጊዜ አትቀየር አትለወጥ ከቶ
በልክህ ያምልክህ ፍጥረትህ ተረድቶ

አንዱም እይጓደል የምትሻው ከኔ
በልክህ አግኘው ያድንቅህ ዘመኔ
ሌላ ምን እላለሁ አንተ ጋር መጥቼ
በገባኸኝ መጠን ላምልክህ አብዝቼ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top