ይኽው ተሰመቶልኝ ጽሎቴ

254

ይኽው ተሰመቶልኝ ጽሎቴ አምሮ ሰመረልኝ ምኞቴ
ይኽው እዘምራለሁ በጌታ ላረገልኝ ብዙ ውለታ
ይኽው እዘምራለሁ ለጌታ ለዋለልኝ ብዙ ውለታ

የመስዋእቴ ቅኔ ምስጋና
የእጅህን ስራ ይመስክርና /2/

ምንስ ልጨምር የቱንስ ላውራ
ሜዳ ሲያደርገው ያንን ተራራ

ዝም አይልም ውለታህን አይቶ
ልቤ ያፈልቃል ምስጋናን ሞልቶ
ልዘምርልህ በአደባባይ
አምልኮ ላብዛ በላይ በላይ

ይኽው ተስመቶልኝ……….

ከወደኩበት ከትቢያ አንስተህ
ሰው አደረከኝ እንዲህ ውብ አድርገህ /2/
ታዲያ ብዘምር ስላንተ ዝና
ሲያንስህ እንጂ መቼ በዛና

አላቋምጥም ላንተ ምስጋና
እጨምራለሁ ገና አለኝ ገና
ከሆንከኝ አቅም ካለ እስትንፋሴ
ታመልክሀለች ሁልጊዜም ነብሴ

አላቋርጥም ላንተ እልልታ
ሁሉ ለሆንከኝ ለአንተ ለጌታ
ከሆንከኝ አቅም ካለ እስትንፋሴ
ታመልክሀለች ሁልጊዜም ነብሴ

አላቋርጥም ላንተ ጭብጨባ
እጨምራለሁ መቅደስ ይግባ
ከሆንከኝ አቅም ካለ እስትንፋሴ
ታመልክሀለች ሁልጊዜም ነብሴ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top