ዛሬም ይላል ማርያም ብጽእት

255

ዛሬም ይላል ማርያም ብጽእት ናት በህይወቷ
ትውልድ አምኖ እግዚአብሔርም ምርጥነቷን
እንደ ቃሉ ሳይቀንስ ሳይጨምር
ያከብራታል ሁልጊዜም የሰው ዘር

ብርቱ የሆነው ስሙም ቅዱስ ነው በእርሷ ታላቅ ስራ አድርጓል
የፍጥረት ጌታ የፍጥረት ንጉስ በማህጸኗ ሊያድር ወዷል
የእግዚአብሔር ጸጋ እንዴት አደላት ዛሬም አምኖ ትውልድ ሁሉ
ብጽእት ይላል እየተስማማ ከቶ ሳይጨምር ከቃሉ

የኢየሱስ እናት ለመሆን በቃች ኧረ እንዴት እንዴት ምስጉን ናት

ከጌታ የተነገርላት ቃል ይፈጸማል እንዳመነች
በነፍሷ ጌታን አክብራዋለች በሱም ሀሴት ታደርጋለች
እንደ እግዚአብሔር ቃል ትውልድ ተረድቶ ማርያም ብጽእት ይላል መጥቶ
የባርያይቱን ውርደቷን አይቶ መንፈስ ቅዱስ በርሷ መጥቶ

ካላማው ጋራ አሰልፏታል ትውልድ ብጽእት ይላታል
ታዛዥ ቅን ልቧ ለእርሱ ባደረ ልኡልም በሀይል ተጸለለ
ኢየሱስ ተቤዥን በእሽታዋ ምሳሌ ሆነ ኑሮዋ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top