ካንተ ወዴት እሄዳለው

256

ካንተ ወዴት እሄዳለው አንተ የህይወት ቃል አለህ
አንተን ትቼስ ምን አተርፋለው አንተ የህይወት ቃል አለህ
ለህይወቴ የምታስፈልጋት አንተ ነህ
ለነፍሴ የምትረባት አንተ ብቻ ነህ

አንተ መልካም እረኛዬ ምንስ አጥቼ አውቃለው
በለመለመ መስክ አድራለው ከረፍትም ውሀ እጠጣለው /2/
ለህይወቴ የምታስፈልጋት አንተ ነህ
ለነፍሴ የምትረባት አንተ ብቻ ነህ

በሞት ጥላ መሀል ብሄድ እንኳን ክፉውን አልፈራም
አንተ ከእኔ እስካለህ ድረስ በሁኔታ አልታወክም /2/
ካንተ ጋር መንገዴ ሁሉ ቀለለ
ያስፈራኝ ያስጨነቀኝ ቀን አለቀ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top