በቃና ዘገሊላ የተገኘሽ ማርያም /2/
በእኛም መካከል ሁኚ ከልጅሽም ጋራ
ዛሬም ከእኛ ጋር ሁኚ ከኢየሱስ ጋራ
ወይኑ አልቆባቸው ግራ ገብቷቸው
የሰርጉ ግብዣ ቀዝቅዞባቸው
ከልጅሽ ጋራ ስለተገኘሽ
የጭንቀታቸው መፍትሄ ሆንሻቸው
እልልታ ሆነ ደስታው ጨመረ
ውሀውን በወይን ልጅሽ ቀየረ
ታምር ተሰራ ድንቅ ተደረገ
አንቺን የያዘ የለም ያፈረ
ፍቅር በረከት እንዲወርድ
ሰላም አንድነት እንዲሰፍን
ድንግል ነይልን ዛሬም ሁሌም
ልጅሽን ይዘሽ ወደ እኛ ቤት
ድንግል ነይ ወደ እኛ ማርያም ነይ ወደ እኛ
አንቺ ነሽ የእኛ ተስፋ በሀዘንም ሆነ በደስታ
ጸብ ክርክር ከእኛ ርቆ
ችግር እርኩሳት ተወግዶ
ስደት ርሀብ ሁሉ ጠፍቶ
አንድ ሆነን ጸንተን እንድንኖር
እመቤታችን ለምኝልን
ጸጋው በእኛ ላይ ይውረድልን
ድንግል ….
