ሞታችንን ሞቶ ህይወትን የሰጠን
የሱስ ካንተ ውጪ ከየትም አይገኝ
ማን አለን ጌታ ካንተ ውጪ
ማን አለን ኢየሱስ ካንተ ውጪ
አንተን ስንበድልህ ከህግህ በመራቅ
ቁስልህን ስንወጋው በሀጢአት በድፍረት
ይቅር ብለኸናል ምህረትን በማብዛት
ይህንን አንረሳም እስካለን በህይወት
ምህረትህን አንረሳም እንዴት እንረሳለን
በህይወት ዘመናችን እንመሰክራለን
እኛም ዛሬ ፊትህ ቆምን ለምስጋና
ሞታችን በህይወት ተቀይሯልና
የሰይጣንን እቅድ በስምህ ተሽሮ
ይኸው ባንተ ጀመርን የሰላምን ኑሮ
ምህረትህን አንረሳም እንዴት እንርሳለን
ነህይወት ዘመናችን እንመሰክራለን
