ዘምራለሁ ላንተ ጌታ የህይወት አዳኝ ነህና
ነፍሴ ወጣች ከመከራ ሌላ የለኝ ባንተው ነውና
ከፍታዬን ወርሻለው በዘመኔ ስላንተ ተርካለሁ
ስምህ ጋሻዬ ሆኖኝ አልፊያለሁ ይኸው ጌታ ባንደበቴ ቅኔ እቀኛለሁ
ይኸው ሞላልኝ ባንተ ስለቴ
ክብር ከፍ በል ኢየሱስ በህይወቴ
ከምልህም በላይ አንተ ድንቅ ነህ
በህይወቴ ስፍራ ልዩ ቦታ አለህ
ከጠላት ፍላጻ የታደከኝ
ተራራው ጫፍ ላይ አንስተህ ነው ያቆምከኝ
የጠላትን ሀይል በክንድህ አድቅቀህ
አሻግረኸኛል ጌታ ማምለጫ ሆነህ
የአብረሃም የይስሀቅ የያእቆብ አምላክ
ባህሩን ሀሩሩን በስምህ አሳለፍክ
እኔም እላለሁ እዘምራለሁ
ያደረክልኝን አምላኬ እመሰክራለሁ
ዝም አልልም ለአንተ እዘምራለሁ /2/
ታድገኸኝ በአይኔ አይቻለሁ
አጽናንተኸኝ በአንተ ጸንቻለሁ
ጋሻ ሆነህ ሰላምን አጊንቻለሁ
ይኸው ልዘምር በፊትህ ቆሜ አለሁ
