ቅዱስ ቁርባን

274

ቅዱስ ቁርባን/2/
የኢየሱስ ስጋና ደም
የሚሰጥ ለአለም ህይወት /2/

1. የሚያድስ የሚለውጥ
የህይወት ቃል ደስታን የሚሰጥ
እርሱ ነው ያለም ሁሉ ቤዛ
እርሱ ነው በደሙ የገዛ

ቅዱስ ቁርባን/2/
የኢየሱስ ስጋና ደም
የሚሰጥ ለአለም ህይወት /2/

2. የፍቅር ሚስጥር ትርጉም ያለው
እጅግ ክቡር ድንቅ ስም ነው
ፍቅር ነው እውነተኛ ፍቅር
በእውነት ለታመኑት ዘውትር /2/

ቅዱስ ቁርባን/2/
የኢየሱስ ስጋና ደም
የሚሰጥ ለአለም ህይወት /2/

3. የሰላም ምንጭ ጌታችን ነው
ጥልቅ ፍቅር ኢየሱስ ነው
ያዳነን የማረከን ስም ነው
ለነፍሳችንም መድሀኒት ነው /2/

ቅዱስ ቁርባን/2/
የኢየሱስ ስጋና ደም
የሚሰጥ ለአለም ህይወት /2/

የቁርባን

Leave a Comment

Scroll to Top