ላደረክልንም ነገር ተመስገን
ስላልሆነልንም ነገር ተመስገን
እግዚአብሔር /3/ ክብር ንገስ ከፍ በል
አይጓደልብህ ላንተ ምስጋና
በሁኔታዎች ሁሉ ልክ ነህና
ስለሆነው ስላልሆነው
ለሚሆነውም ነገር ተመስገን
ተመስገን ጌታ ስለ ስጦታህ
ክብር እንልሀለን ጠዋትም ማታ
አለትን ሰንጥቀህ ውሀን አጠጣኸን
በምድረ በዳ መናን አንተ መገብከን
በጨለማ ውስጥ ብርሀን
የሆንክልን አምላክችን ተመስገን
ምስጋናችን ነህ ባለውለታ
ተወደስ እግዚአብሔር ተመለክ ጌታ
