ኢየሱስ የህወቴ መድህን ነህ
አንተ ልቤን ያሳረፍክ
ዘላለም ላንተ ልስገድ ልገዛልህ
አምላክ ነህ አምልኮ የሚገባህ ጌታ
ሁሉን ገዝተሀል
ዙፋንህ ስር ቆሜ ክብርን አሰጥሀለሁ
ባባትህ ቀኝ በክብር ተቀምጠህ
በስልጣንህ ትገዛለህ
ላንተ ስግደት አምልኮ ይገባል
ከፍ ላድርግህ ለዘልአለም
አመልክሀለው /3/ ለዘልአለም /4/
ኢየሱስ ልቤን የማረከው አዳኝ
ስራህ ድንቅ ነው
ፍቅርህ ልቤን ሞላው እኔም እወድሀለሁ
ቃላቶች ሊገልጹት ኣልቻሉም ውስጤን
በእውነት ወደድኩህ
ላንተ ያለኝ ፍቅር እጅግ እጅግ ታላቅ ነው
ጧትም ማታም ኣንተን አስባለሁ
ስራህንም አደንቃለሁ
ፍቅሬን ልገልጽ እድል ስላገኘሁ
እኔም አልኩኝ እወድሀለሁ
እወድሀለሁ /3/ ለዘላለም /4/
