ይሆናል በእርሱ ይሆናል
ይሳካል በእግዚአብሔር ይሳካል
ዛሬ ያስጨነቀ ያሳሰበኝ
ቀን አለው በእርሱ ይከናወናል
ለሀሳብ ለጭንቀት አልሰጥም ኡኡታ
ይልቅ ለእግዚአብሔር ነገርኩት ለጌታ
ሁሉንም ሰጥቼው ለእርሱ አልከበደው
አከናወነልኝ ሸክሜን አቀለለው
ተውኩለት ለጌታ እርሱ ያውቅበታል
ለእኔ ሚጠቅመኝን ሚበጀኝን ያውቃል
ነገርኩት ሁሉንም በመልኩ ሰራልኝ
ያስጨንቀኝ ጠፋ አደላደለልኝ
ልቤ ቢዝልብኝ ጉልበት ቢከዳኝ
ቢታወርም አይኔ ጨለማ ቢውጠኝ
አልገደበኝ ድቅድቅ ለጌታ ለመንገር
የጭንቀቴን ገመድ በደሙ ለማሰር
የምን ለቅሶ ሀዘን ለእኛስ ጌታ አላ
ሀይሉ ኣባታችን ከእኛ ዞር አላላ
ሮጠን መጠጊያችን እርሱ አለታችን
የጭንቃችን ደራሽ አጋር ጓደኛችን
