ይገባሀል

279

በዘላለም ዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ
ሁሌ የምትጸና ገገር ሀያል ነህ
ባገዛዝህ ተማርከናል ወደንሀል
ልናከብርህ ልንገዛ ፈቅደናል ተባረክ
ተባረክ ዛሬም ተባረክ
ተባረክ ነገም ተባረክ

ተባረክ ሁሌም ተባረክ አሜን

እንደ ፍቅርህ እንደቸርነትህ መጠን
አዎ ያደርከው ሁሉ መልካም ነገር
እንደ ቀድሞ ዘመን ሁሉ ያዳንከን
ለክብርህ ልንቆም አድርገህ ቀባኸን ተባረክ

አይነስብህ ጌታ አይነስብህ ምስጋና /2/

ይብዛልህ ላንተ ይብዛልህ ጌታ
ልዩ ለሆንከው ሀያል ገናና
ይብዛልህ ላንተ ይብዛልህ ጌታ
ለክብርህ ይሁን ይኸው ሽብሸባ

ላንተ ክብር ይሁን ላንተ
ላንተ ሞገስ ይሁን ላንተ

ከፍ በል አንተ በማደርያህ ላይ ያለኸው
ከፍ በል አንተ በዙፋንህ ላይ ያለኸው
ከፍ በል ‹‹ በመቅደስህ ውስጥ
ከፍ በል ‹‹ በሰማያት ላይ ያለኸው
ላንተ ክብር ይሁን ላንተ
ላንተ ሞገስ ይሁን ላንተ

ብዙ ምስጋና ይዤ እገባለሁ አንተን ለማምለክ መቅደስህ እገኛለሁ
ይኸው ምስጋና በዝማሬዬ ለክብርህ ይሁን ላንተ ጌታዬ
ይኸው ምስጋና አበዛለሁኝ ቅኔን በፍቅር እቀኛለሁኝ
ከፊትህ ቆሜ እያሸበሸብኩ ያማረ ዜማ አቀርባለሁኝ
ከፊትህ ቆሜ እያጨበጨብኩ በደስታ ሆኜ እዘላለሁኝ
ላንተ ክብር ይሁን ላንተ
ላንተ ሞገስ ይሁን ላንተ

ይገባሀል /8/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top