የእግዚአብሔርን ስራ ግሩም ነው በሉት

280

የእግዚአብሔርን ስራ ግሩም ነው በሉት
የሱን እፁብ ስራ ተግባሩን ኣድንቁት
ከምንም አንስቶ እዚህ ያደረሰን
አመታትን ቆጥሮ ዘመን ለጨመረን

ይኸው ምስጋና /2/
ይኸው ዝማሬ /2/
ይኸው አምልኮ
ይኸው ውዳሴ /2/

እንዘምራለን ለክብርህ ያማረ ዜማን አንሰዋልህ
ምስጋና እንደ ነዶ እናቅርብልህ እንቀኝ በመዝሙር እንስገድልህ
የእግዚአብሔርን ስራ ግሩም ነው በሉት ግሩም ነው በሉት /4/

በአደባበይ መሀል በሸንጎ በቅኔ
መስክሩ ሁላችሁ እያላችሁ የኔ
አምልኮ ይብዛለት ውዳሴ ይድረሰው
ኑ እንዘምርለት አልሻዳይ ለሆነው
ይኸው ሽብሸባ /2/
ይኸው ጭብጨባ /2/
ይኸው እልልታ
ይኸው ሙገሳ /2/

ግርማ ሞገስህ ድንቅ ነውና
ምህረትህም ከጥንት እስከ አሁን ነውና
መአዛው እንዲያውድ እጣን ይሁንልህ
ጌታ አንተ ውደደው በክብር ይድረስህ

የእግዚአብሔርን ስራ ግሩም ነው በሉት ግሩም ነው በሉት /4/
ምስጋና /2/ ይኸው
ዝማሬ /2/ ይኸው
አምልኮ/2/ ይኸው
ውዳሴ /2/ ይኸው
ይኸው ሽብሽባ /2/
ይኸው ጭብጨባ /2/
ይኸው እልልታ
ይኸው ሙገሳ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top