የገረመንፍቅር

283

ገረመን/3/ ፍቅር የኢየሱስ ብቻ ነው

ገረመን/2/ ፍቅር እንዲህ ነው
መውደድ እንዲህ ነው
ኢየሱስ ለኛ የከፈለው

ከሰማያት ክብሩን ጥሎ ወርዶ
ብርሀንን አሳየን ስለኛ ተዋርዶ
ፍቅሩ እንዲህ እንዲህ ጥልቅ ነው
ነፍሱን ለሀጥያት ካሳ የሰጠው

ትሁት ነው ቃላት የማይገልጸው
በሸላቾቹ ፊት ዝም ያለው
ክብሩን ሀይሉን ውበቱን አጥቶ
መውደዱን አሳየን ነፍሱን ሰጥቶ
ኦ ገረመን ኦሆ ደነቀን ኦሆ ገረመን
የመውደድ ጥግ በኢየሱስ አይተን /s.a.t.b.sh/

በፍቅሩ ጥልን ከኛ አራቀ
የሞት መውጊያ ሁሉ ደቀቀ
በመስቀል እጆቹን ዘርግቶ
እንዲሁ ወደደን ለኛ ሞቶ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top