ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ ሞቶ ሞትን ረገጠ/2/
በመቃብር ውስጥ ላሉት የዘልዓለም እረፍትን ሰጣቸው
መቃብሩን ፈነቃቅሎ ተነሳልን
ሞትን ድል አረገለን /2/
በሞቱ ህይወትን ዘራብን
ሞትን ድል አረገልን /2/
የትንሳኤው ጌታ የፋሲካው ንጉስ
ከሞት በላይ ሆኖ ድል አረገ ኢየሱስ /2/ ተነሳ
ሞት ሆይ መውጊያህ ተሰብሯል
ማህተሙን ፈቶታል /2/
ሞታችን በውርደት ሞቷል
የጥልን ሐይል ሰብሮታል /2/
የነሀሱን በር ሰባብሮ ክብርን ሞገስንም ደርቦ
ለዘልዓለም እያበራ ይኖራል ከእኛ ጋራ /2/ ተነሳ
ተነሳ በወይን እንደተኛ
ተነሳ መስሎ ያሸለበ
ተነሳ ታሪክን ሊቀይር
ተነሳ ክርስቶስ ተነሳ
ተነሳ በወይን እንደተኛ
ተነሳ መስሎ ያሸለበ
ተነሳ ታሪክን ሊቀይር
ተነሳ ክርስቶስ ተነሳ
