ቅዱሱ ማደርያህ ክፍት እያለ
የምስክር ድንኳን ኑ ግቡ አለ
የቅዱስ ስሉስ የጸባኦት
የቅዱስ ሀያል ህያው የማይሞት
በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው
ማዳን ለእርሱ ብቻ ቅዱስ ለሆነው
ማደርያው ገቡና እስቲ ከፍ አድርጉት
በመቅደሱ ለእርሱ እልል በሉለት
ብጹአን ቅዱሳን ስምህን የሚወዱ
ታላላቅ ታናናሽ ታላላቅ ላንተ የሚሰግዱ
ይኸው ወግነናል ከሚወዱህ
በድንኳንህ ደጃፍ ለሚፈልጉህ
አሜን በውዳሴ በገናናነት
ምስጋናና ክብር ሀይልም ከብርታት
ለአምላካችን ለዘልአለም ይሁን
በማደርያው በቅድስተ ቅዱሳን
አንትን የማያከብር አረ እረሱ ማነው
ላንተስ የማይሰግድ ማን የፈጠረው
መጥተናል ልንሰግድልህ በፊትህ
በሃሴት በእልልታ ልናወድስህ
እልል በሉለት እልል እልል አሜን
አሜን አሜን አሜን
