አቤቱ ጌታዬ ምሕረትህ የበላይ

290

አቤቱ ጌታዬ ምሕረትህ የበላይ
አቻ የሌለህ ነህ በምድር በሰማይ /2/
እኔ ላንተ ጌታ እኔ ላንተ ጌታ እቀኛለሁ
ምስጋናዬን ላንተ ዘውትር አቀርባለሁ
ሀሌሉያ /6/

በመዝሙር በዜማ አባት ላመስግንህ
ጌታ አስገርሞኛል ያንተ ድንቅ ስራ /2/
ሳልቆጥብ ልዘምር ለታላቁ ክብርህ
ስምህን ላክብረው ለገናናነትህ /2/

ሁል ጊዜ ስምህን ክበር እለዋለሁ ሁሉን ድል ያረኩት ባንተ እርዳታ ነው /2/
አባቴ ውለታህን መቼ እዘነጋለሁ
ማንነቴን ለወጥከው ሁሌ አከብርሀለሁ

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ላንተ ዕልል ልበል አስደናቂ ነገር አድርገህልኛል /2/
ካንተ የሚወዳደረ ከቶ ማንም የለም
አንተ ለኔ ያቀድከው ሊቆጠር አይችልም /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top