በፊትህ ወድቀናል ምህረትህን ፈልገን
ልባችንን ቀደን በእውነት ተፀፅተን
አቤቱ አስበን ይቅር በለንና
በምህረትህ ጎብኘን ፊትህን መልስና
ጌታ ለሕዝብህ ራራ /3/
ጌታ ለኢትዮጵያ ራራ /3/
ኃጥያታችን በዝቶ አንተን አሳዝኗል
በምድር ተቅበዝባዦች ባዛኞች ሆነናል
ደከመን ሰለቸን እንዲህ አይነት ሕይወት
በቃ በለንና ጎብኘን በምህረት
የሰራነው በደል ቁጥር ስፍር የለው
እባክህን ጌታ እርሳው አትቁጠረው
የኃጥያታችን ጉድፍ በደምህ አንፃና
ዳግም ሰው አድርገን ይቅር በለንና
የምህረት አምላክ መማር አይሰለቸው
ዛሬም ኢትዮጵያን እያት በምህረትህ
ተስፋዋ አንተ ነህ እፎይ ምትልበት
ችግር መከራዋን የምትረሳበት
