1. ሁሉን የምትገዛ በገናናው ክብርህ
እግዚአብሔር አምላክ ላንተ እንስገድልህ
በቃልህ ትዕዛዝ አለምን የፈጠርክ
ጉልበት ሁሉ ላንተ ለሥምህ ይንበርከክ
ሀሌ ሉያ /4//2X
2. ሁሉን ትረታለህ ኃይል አለ በክንድህ
ኦ! ጌታ ድንቅነህ ማነው የሚመስልህ
ቅዱስ ነህ እያልን እናመልክሀለን
በስልጣንህ እዘዝ ታላቅ ስምህ ይግነን
ሀሌ ሉያ /4//2X
3. አንተ ብቻ ጌታ አንተ ብቻ ንጉስ
አቻ አይገኝልህ ለዘላለም ቅዱስ
አንተ ስትገለጥ በክብር ስትቆም
ሊቃወም የሚችል አንድም ኃይል አይኖርም
ሀሌ ሉያ /4//2X
4. ማለዳ ማለዳ ያንተ ታማኝነት
አዲስ ነው ብዙ ነው ይገባሀል ስግደት
ዝማሬና እልልታ ይሙላው ጉባኤውን
በፅድቅ ተመላለሰ አክብረው ስምህን
ሀሌ ሉያ /4//2X
5. ከቶ ትዋሽ ዘንድ እንደ ሰው አይደለህ
ቃልህ የፀና ነው በምን እንመስልህ
ሥግደታችን ይኸው በመንፈስ በእውነት
ከዙፋንህ ይድረስ አንተው ክበርበት
ሀሌ ሉያ /4//2X
