መልካምን አድርገሀል ለኔ
ስትረዳኝ አይቻለሁ በአይኔ
ውለታህ እኔ አለብኝ እና
ቆሜያለሁ ፌትህ ለምስጋና /2/
ምስጋና /3/ አምላኬ ይገባሃልና /2/
1. ለኔ ያደረከው ግሩም ነው ድንቅ ነው
ከአይምሮዬ በላይ በቃል የማልገልፀው
ለውለታህ ምላሽ እኔ አለኝ የምለው
ሌላ ነገር የለኝም ምስጋና ብቻ ነው
ምስጋና……
2. መልካምነትህን ችዬ ምገልፅበት
አንድም ቃላት የለኝም የምመጥንበት
ግን እኔ አልሻም ማለፍ በዝምታ
አመስግን ይለኛል የበዛው ውለታ
