ይሄ ነው እግዚአብሔር

-

አዝ. ይሄ ነው እግ/ር ለኔ የደረሰው
ከጠበኩት በላይ ድንቅን ያደረገው
ስለዚህ በፊቱ ምስጋናን እሰዋለሁ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ /2/

ምን እላለሁ ምስጋናን ለእርሱ እሰጣለሁ
ምን እላለሁ ምስጋና አበዛለሁ /2/

1. ሃይ ብትወጣ በስተምስራቅ በኩል
ሲመሽባት ደግሞ በስተምዕራብ ብትሆን
ማንም አይገረምም በነዚህ ድርጊቷ
ወግና ስርዓቷ ነው ከጥንት ፍጥረቷ

አንድ ቀን በደቡብ ብትወጣ በድንገት
ሲመሽባት ደግሞ ሰሜንን ብትመርጥ
ያኔ እንግዳ ነገር ለሁሉም ይሆናል
ለእኔ ግን አምላኬ ከዚህ በላይ አርጓል

ጉድ ተባለ ሆነ ያልተጠበቀ
ተሰራልኝ ባለም ያልታወቀ
እርሱም ይህ ነው የመዳኔ ነገር
ከሞት የመትረፌ አያልቅም ቢነገር /4/

አዝ. ይሄ ነው እግ/ር ለኔ የደረሰው
ከጠበኩት በላይ ድንቅን ያደረገው
ስለዚህ በፊቱ ምስጋናን እሰዋለሁ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ

ምን እላለሁ ምስጋናን ለእርሱ እሰጣለሁ
ምን እላለሁ ምስጋና አበዛለሁ /2/

2. እንዲህ በቀላሉ እንደዋዛ ታልፎ
ሊተው አይቻልም አያስቀምጥ አርፎ
ውስጡ የተቀመጠ ምህረቱ የገባው
ይነዘንዘዋል ቀን ከሌት ውለታው

ቢያቅተኝ ቢቸግረኝ ዝም ማለት
ጉባኤ መጣሁኝ ህዝቡ ባለበት
እኔ እያስታወስኩኝ ያረገውን ስራ
አምልኮን ልሰዋ ከጉባኤው ጋራ

የገባው ሰው የተደረገለት
ያላስቻለው ውለታው ያለበት
ይነሳና አብሮኝ ከፍ ያድርገው
ምህረትና ፍቅሩ እስከዘላለም ነው /4/

አዝ. ይሄ ነው እግ/ር ለኔ የደረሰው
ከጠበኩት በላይ ድንቅን ያደረገው
ስለዚህ በፊቱ ምስጋናን እሰዋለሁ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ

ምን እላለሁ ምስጋናን ለእርሱ እሰጣለሁ
ምን እላለሁ ምስጋና አበዛለሁ /2/

3. በመስቀል ላይ ለኔ የሰራውን ስራ
ቀንም ሆነ ሌሊት ሁልጊዜ ባወራ
ቃላት አየበቃኝም ዓረፍተ ነገሮች
እንጂ የርሱ ስራ አያልቅ እንደሌሎች

እልልታና አምልኮ ላምላኬ ሳላስቀር
በምስጋና ፊት ከመቅረብ በስተቀር
ሌላ ምን ምርጫ አለኝ ለርሱ የምሰጠው
ገና ጨማምሬ ምስጋናን ሰዋለሁ

መቼ ያልቃል ቢወራ ቢወራ
ተናግሬ መቼም አላበቃ
እርሱም ይህ ነው የመዳኔ ነገር
የመስቀሉ ሥራ አያልቅም ቢነገር /2/
የኢየሱስ ሥራ አያልቅም ቢነገር /2/

አዝ. ይሄ ነው እግ/ር ለኔ የደረሰው
ከጠበኩት በላይ ድንቅን ያደረገው
ስለዚህ በፊቱ ምስጋናን እሰዋለሁ
ተመስገን ተመስገን ተመስገን እላለሁ

ምን እላለሁ ምስጋናን ለእርሱ እሰጣለሁ
ምን እላለሁ ምስጋና አበዛለሁ /2/

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top