ካንተ ያልሆነልኝ

-

ካንተ ያልሆነልኝ ያልሰጠኸኝ ምን አለ
ሳትሰራው ሳትፈፅመው የቀረ
ሁሉንም ውብ አድርገሃል
እግዚአብሔር ምስጋና ይገባሃል /2/

አፌ በምስጋና ላይ ምስጋና
ልቤም በዝማሬ ላይ ዝማሬ
ይጨምራል እንደገና /4/

1. ለሆነልኝ ሁሉ ከአንተ ላገኘሁት
ለሰጠኸኝ ነገር ለተቀበልኩት
ምን አለኝ የምልህ ምላሽ የሚሆነኝ
ከማመስገን በቀር እስቲ ምን ልናገር

ተመስገን /2/ ተባረክ /2/ /2/

ካንተ ያልሆነልኝ ያልሰጠኸኝ ምን አለ
ሳትሰራው ሳትፈፅመው የቀረ
ሁሉንም ውብ አድርገሃል
እግዚአብሔር ምስጋና ይገባሃል /2/

አፌ በምስጋና ላይ ምስጋና
ልቤም በዝማሬ ላይ ዝማሬ
ይጨምራል እንደገና /4/

2. አፌን ገና ስከፍት ስላንተ ላወራ
እምባ እየቀደመኝ ከምስጋና ጋራ
ጥያቄዬን ሁሉ ከውስጤ አወጣለሁ
አባ ደግነትህን ሳይ እረሳዋለሁ

ተመስገን /2/ ተባረክ /2/ /2/

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top