ጥበብን መረጥኩኝ

-

ጥበብን መረጥኩኝ ሌላ ሁሉን ጠላሁ
ሀ : ብዬ ልጀምር እግዚአብሔርን ፈራሁ

1. ደስታን ስትፈልግ ኑሮህ አንዲሟላ
ጥበብን ፈልጋት አትሂድ ወደሌላ
የርሷ መጀመሪያ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ነው
ስገደትና አምልኮ ሁሉ የሚገባው

2. ጥበብ ማስተዋል ናት ከሁሉ የምትልቅ
ብልህን የምትወድ ምኞችን የምትርቅ
ሁሉን በማስተዋል እውቀትህ እንዲበዛ
ጥበብን ውደዳት ለአምላክም ተገዛ

3. ጥበብ በጎነተ ናት ለሁሉ የምትሰጥ
ርኅራሄ ያላት ጸድቅና የምታበልጥ
ጥበብን ብትወድ ተካፍለህ ብትበላ
እግዚአብሔር ያደርጋል ኑሮህ የተሟላ

4. ጥበብ አውነትና ታማኝነት ናቸው
እንደ ዓይንህ ብሌን ጠንቅቀህ ያዛቸው
ቅንነትን ብትወድ አውነት ብትናገር
ሁሌ ይረዳሀል አምላከህ አግዚአብሔር

5. በዚህ ዓለም ኑሮ ስንቱን አሳሰፍኩኝ
ሁሉንም አየሁት ግን ምንም አጣሁኝ
ጥበብን አረኳት ብቸኛ ምርጫዬ
የሕይወቴ መድኀን ለኔስ መመኪያዬ

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top