ማደሪያህ ይሙላ ምስጋና
ተመለክ አንተ ገናና
መቅደስ ይሙላ አምልኮ
ወደር የሌለህ ነህ እኮ
1. አሕዛብ ተደነቁ አምላካችሁ የት ነው
የኛ አምላክ መኖሪያ ሰማይም ምድርም ነው
ከጨለማው ግዛት ያወጣን እሱ ነው
እንላለን ዛሬም መታመኛችን ነው /2/
2. የአማልክት አምላክ ስሙ እጅግ ገናና
ታምርን የሚያደርግ አውቅ ባለዝና
ምድርን በውሃ ላይ በቃሉ ያጸና
ለእግዚአብሔር ይብዛለት ይጨመር ምስጋና /2/
3. አይገርመን አይደንቀን ተአምርን ለምደናል
የሞተ ሲነሳ በአይናችን አይተናል
በድንቅ አሰራሩ አጅግ ተገርመናል
ከአንደበታችን ቃል ልቆ በልጦብናል /2/
4. ዛሬም አላበቃን ታሪኩን ተርከን
ሕያው ነው ዘላለም የሌለበት እንከን
ቅዳሴ ይቀደስ እጣኑም ይታጠን
ጀማመርነው እንጂ አልጠገብን አምልከን /2/
ምስጋና ይብዛለት ምስጋና /3/
አምልኮ ይብዛለት አምልኮ /3/
ዝማሬ ይብዛለት ዝማሬ /3/
