ወዳጄ ነህ አንተ የዓይኔ ማረፍያዬ
መመኪያዬ አንተ የእኔ ስጦታዬ 2x
1. ነፍሴን ማርከህ በፍቅር አሳርፈኸኛል
ግሩም ምክርህ ልቤን ሞልቶ ሰላሜ ሆኖልኛል
በምሕረትህ ባለፀጋ ሁሉ በሁሉ የሆንክ
ማን እንዳንተ ለእኔ ክብሬ የውስጥ እርካታዬ
አለልኝ ለኔ አለልኝ በቃ
አለልኝ ለኔ የነፍሴ ጌታ
አንተ ነህ ለኔ አንተ ነህ በቃ
አንተ ነህ ለኔ ያይኔ ማረፍያ
2. ፍቅርህን አግንነህ እኔን አስበሃል
ከሃዘን ከብስራት ልቤን ጋርደሀል
ፊትህን እያየው ዝማሬን ላሰማ
አለልኝ እላለው ፍጥረት ሁሉ ይስማ 2x
አለልኝ ለኔ አለልኝ በቃ
አለልኝ ለኔ የነፍሴ ጌታ
አንተ ነህ ለኔ አንተ ነህ በቃ
አንተ ነህ ለኔ ያይኔ ማረፍያ
