1. ብትፈቅድ ፈጠርከኝ አልመጣሁ በራሴ
ክቡር ስጦታህ ነው ስጋዬና ነፍሴ
ምን ከኔ ሆነና ምኔና ላውራው ለሰው
ሰው ላረገኝ ጌታ ምስጋና ይድረሰው /3/
አዝ. ምን ታሪክ አለና አንተው ነህ ታሪኬ
ቁም ነገሬ ሁሉ የርካታዬ ልኬ
ምኔን ላውራው ለሰው ምን አደረግኩ በራሴ
ኃይል እውቀቴ ቢባል አንተው ነህ ታሪh /3/
2. በልቶ ጠግቦ ማደር የዕለት የዕለቱን
ደስታን ከዓለም መሻት የማይሆነውን
አርቆ አለማሰብ መጨረሻዬን
ይህ ነበር ታሪኬ ሳላውቀው ጌታን እርሱን /3/
3. በውድቀቴ ሰዓት አቅፎ ባያነሳኝ
የሃጥያቴን ቁልል ከኔ ባይገፍልኝ
ተሸክሜው ቢሆን ያ ሁሉ ክፋቴ
ሃዘኔ በርክቶ ባቀረባት/ባፈጠናት ሞቴን /3/
4. መልካም መስያቸው ያዩኝ ተደሰቱ
እንደ አህያይቱ መሆኔን ቢስቱ
እየሱስ በእኔ ሆኖ ቀርቶ መታሰሬ
ሃፍረቴም ተረሳ ጌታ ሆኖኝ ክብሬ
እየሱስ ሆኖኝ ክብሬ ጌታ ሆኖኝ ክብሬ
