ከክፉ ሰውረን

-

አዝ. ከክፉ ሰውረን፣ ከክፉ ሰውረን /2/

1. ፈውስን ለድውያን ሕይወትን ለሙታን
ምሕረትን ለኃጥአን ለጨለማ ብርሃንን
መስጠትን ዓላማህ ተልዕኮህ አድርገህ
የማዳን ሥራህን በብቃት ተወጥተህ
ከክፉ መሰወር ነው ለካስ ባሕሪይህ
ያንተ መጠሪያህ

2. ከክፉ ሰውረን ብለን እንድንጸልይ
ያስተማረን ልጅህ የሁሉ የበላይ
በግልጽ አውቆት ኖሯል ስላለው አታላይ
ልብን ከአምላክ የሚያርቅ የሚሆን ከፋፋይ
ጨለማን የሚያሰፍን መንግሥትህ እንዳይታይ
መንፈስህን የማያሳይ

3. የእኔ ብቻ የሚል ግፊት አስሮ ይዞኝ
እንዲያው በጭፍኑ ጥማቴን ስል ሙጥኝ
ማመዛዘን ራቀኝ ሁሉ ጨለመብኝ
ጥበቃህ አንድ አፍታ ከጎኔ ቆሞልኝ
ከክፉ ሰውረህ ለፅድቅ አበቃኸኝ
በጎውን ጠቆምከኝ

የምስጋና

Leave a Comment

Scroll to Top