1. የበዓል

ተመስገን, መልካም ጋብቻ, ይህች አጥንት, ይባረክ, እኛ እናውቅሃለን, ደስም አለን, ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች, ክብር እንዴት ይነሳት, ብዙ ብዙ ነው, ይኸው ተሰምቶልኝ ፀሎቴ, ክብር ዛሬም እንጨምር , ቸር እግዚአብሔር ሆይ, በአንድ ሃሳብ ተስማሙ, ያለው ይሆናል, ገናና ነው, አይጥልም

ተመስገን
ከደጅህ ስንደርስ በባረካት እለት
ላፋችን ሚቀናን ክበርልን ማለት  /2/
ካረክልን ጋር ስናወዳድረው
ምስጋናም ቢሆን እጅግ ጥቂት ነው   /2/

ተመስገን /8/

1. ለሆነልን ሁሉ ኖረን በህይወታችን
ከልጅነት ወራት እስከ ጉብዝናችን
ዝም ብለን ቀርቶ እንዲያው ብለን ችላ
አመስግነን እንኳን ልባችን በሞላ /2/

ተመስገን /8/

2. ጥንትም ባንተ ነበርን ዛሬም ባንተ አለን
የሰጠኸን ሲታይ ምን አለ የጎደለን
እንደመዝሙረኛው እንደልብህ ዳዊት
ማመስገን ሆኖናል የተረፈን መክሊት /2/

ተመስገን /8/

3. ምክንያት አንሻም አንተን ማመስገኛ
መኖርክን ማመን በቂ ሆኗል ለኛ
ማየትን በሚሻ በምልክት ዘመን
ሳናይ አምነንሀል አምላክ ሆይ ተመስገን /2/

ባንተ ነው (ሴ)  ሞልተን ብንታይ
ሞገስህ(ሴ)   በክብራችን ላይ
ያበራው(ሴ)   ከዘመን ዘመን
ባንተ ነው ጌታ ሆይ ተመስገን

ባንተ ነው(ወ)   ስኬት የቀናን
ስንታይ(ወ)   ፀጋህ የሞላን
ያበራው(ወ)   ከዘመን ዘመን
ባንተ ነው ጌታ ሆይ ተመስገን

ተመስገን /8/

 

መልካም ጋብቻ
1. ግብዝነት በሌለው ፍቅር ወዶናልና
እርስ በርሳችን እንድንዋደድ አዞናል
ኑሮአችሁ በጌታ ፀንቶ እንዲኖር
ታምናችሁ ቁሙ በጌታ ፍቅር

መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ
በኑሮአችሁ ሁሉ መንፈሱ ይምራችሁ
ለዚች ቀን በሰላም ያደረሳችሁ
ህያው እግዚአብሔር ይክበር በኑሮአችሁ

2. ሰይጣን ለተንኮሉ ወጥመድ ቢዘረጋ
እንዲያው ተፍጨርጭሮ መከራ ቢያንጋጋ
ያመናችሁት አባት ከለላ ነውና
ብቻ ስሙን ጥሩ ሁሌ በምስጋና

መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ
በኑሮአችሁ ሁሉ መንፈሱ ይምራችሁ
ለዚች ቀን በሰላም ያደረሳችሁ
ህያው እግዚአብሔር ይክበር በኑሮአችሁ

3. መሰረታችሁን በአለት ላይ ገንቡ
በመልካም በመኖር ወደ እርሱ ቅረቡ
ጌታን ተከተሉ ፍቃዱን ፈፅሙ
መልካምን በማድረግ በወንጌሉ ቁሙ

መልካም ጋብቻ ይሁንላችሁ
በኑሮአችሁ ሁሉ መንፈሱ ይምራችሁ
ለዚች ቀን በሰላም ያደረሳችሁ
ህያው እግዚአብሔር ይክበር በኑሮአችሁ

 

ይህች አጥንት
ይህጭ አጥንት ከአጥንቴ ናት
ጌታ ቤቴ ከመለሳት
አይሁንብኝ ጎኔ ባዶ
ካደረገው ጌታ ይህንን ወዶ /2/

በመንፈስና በእውነት ይሁን የጸና በዓለት/2/
መልካም ጋብቻ ይሁን /4/

የደስታ የተድላ በፍቅር የተሞላ
የሁለት አንድነት ያድርገው ጌታ
ይህንን ጥምረት /2/

1. እግዚአብሄር ያፅና በድል ፍፃሜ
እንደ አብርሃም እንደሳራ እድሜ
ፍጹም ተሞልቶ መተሳሰብ
ይሁን ይህ ጥምረት ያለው መስህብ /2/

የደስታ የተድላ በፍቅር የተሞላ
የሁለት አንድነት ያድርገው ጌታ
ይህንን ጥምረት

2. ኑሮ ቢሞላ ኑሮ ባይሞላ
እግዚብሄር ብቻ ይሁነን ተድላ
ሁሉም መልስ አለው ካሉ በጌታ
ቃል ኪዳኑ ግን እንዳይፈታ

የደስታ የተድላ በፍቅር የተሞላ
የሁለት አንድነት ያድርገው ጌታ
ይህንን ጥምረት

 

ይባረክ
ይባረክ /3/ በአንተ ማረግ
ይቀደስ /3/ በአንተ ሞገስ /2/

ቀድስልን ይህንን ጋብቻ እግዚአብሄር
የፍቅር እሳት ይውረድ የፍቅር
በሙሽሮች በዓል በክብር
የፍቅር እሳት ይውረድ የፍቅር
በልጆችህ መሀል በክብር

እናምናለን(ወ)   አዳም እፎይ አለ
እናምናለን(ወ)    ሄዋንም አረፈች
እናምናለን(ወ)    በእጅህ ተይዘው
ተሸላለሙ በምስጋና ፀንተው

እናምናለን(ሴ)   በአንተ የታመነ
እናምናለን(ሴ)   አንተን የሚፈራ
እናምናለን(ሴ)   አንዲህ ይባረካል
በአደባባይ ይህን ይተርካል

ቀድስልን ይህንን ጋብቻ እግዚአብሄር
የፍቅር እሳት ይውረድ የፍቅር
በሙሽሮች በዓል በክብር
የፍቅር እሳት ይውረድ የፍቅር
በልጆችህ በዓል በክብር

እናምናለን(ሴ)   በአብርሐም አምላክ
እናምናለን(ሴ)    ሳራን ባከበረ
እናምናለን(ሴ)    ይህ ቅዱስ ጋብቻ
ፍቃዱ ሆኖ በፊቱ እንዳማረ

እናምናለን(ወ) ወዳጅ ዘመድ ሲማር
እናምናለን(ወ)  ቤተሰብ ሲኮራ
እናምናለን(ወ)  የእግዚአብሔር አላማ
ተከናወነ ተብሎ ሲወራ

ቀድስልን ይህንን ጋብቻ እግዚአብሄር
የፍቅር እሳት ይውረድ የፍቅር
በሙሽሮች በዓል በክብር
የፍቅር እሳት ይውረድ የፍቅር
በልጆችህ በዓል በክብር

 

እኛ እናውቅሃለን
እኛ እናውቅሀለን ስራህን ስላየን
እኛ እናውቅሀለን ስትረዳን ስላየን
እኛ እናውቅሀለን ክንድህን ስላየን
እኛ እናውቅሀለን ሀይልህን ስላየን

ጌታ ድንቅ ነህ አቻ የሌለህ
ኸረ አንተ ድንቅ ነህ ወደር የሌለህ /2/

1. ከስንት ውጣ ውረድ ማለፍ ከማንችለው
አስበን ተጨንቀን ከማንወጣው
ባንተ ተደግፈን አርነት ወጥተናል
ሀይልህን ልናውጅ በፊትህ ቆመናል

ጌታ ድንቅ ነህ አቻ የሌለህ
ኸረ አንተ ድንቅ ነህ ወደር የሌለህ

2. ካንተ ምንቆጥበው ምንም ነገር የለን
ልንሰጥህ ወደናል ያለንን አውጥተን
አንተው በሰጠኸን ልሳን ባርከኸን
ለአንተ ለአምላካችን እንዘምራለን

ጌታ ድንቅ ነህ አቻ የሌለህ
ኸረ አንተ ድንቅ ነህ ወደር የሌለህ

3. አንተን ታምነን ወጥተን ስንት ድንቅን አየን
እቅዳችን ሰምሮ ልባችን ደስ አለን
እጃችን በአፋችን ጭነን ተገርመናል
በስራህ ልዩ ነህ ግሩም ነህ ብለናል

ጌታ ድንቅ ነህ አቻ የሌለህ
ኸረ አንተ ድንቅ ነህ ወደር የሌለህ

4. ከገመትነው በላይ ሆነብን ውለታህ
አውርተን አያልቅም ያንተን መልካም ስራ
እንደተገረምን አለን እንኖራለን
ስላንተ መግለጫ ሚመጥን ቃል አጥተን

እኛ እናውቅሀለን ስራህን ስላየን
እኛ እናውቅሀለን ስትረዳን ስላየን
እኛ እናውቅሀለን ክንድህን ስላየን
እኛ እናውቅሀለን ሀይልህን ስላየን

ጌታ ድንቅ ነህ አቻ የሌለህ
ኸረ አንተ ድንቅ ነህ ወደር የሌለህ

ደስም አለን
እግዚአብሄር ታላቅ ነገር አረገልን ደስም አለን /2/
ደስም አለን /4/

ስሙ ይመስገን ምን ይባላል ሌላ
ያማረ እልልታ መቅደሱ ይሞላ
ይክበር ይመስገን ምን ይባላል ሌላ
ያማረ እልልታ መቅደሱ ይሞላ

1. ከዘመናት በፊት ይኼ ቀነ ነበረ
እግዚአብሄር ሲሰራው እጅግም ያማረ
እግዚአብሄር ሲሰራው ነበረ ያማረ /ወ/
አዲስ ውበት ይዞ ዛሬ ከተፍ አለ
እግዚአብሄር ተናግሮ ከልካይ ሰው ማን አለ
ሁሉ በእርሱ ሆኖ ደስታችን አየለ /ሴ/

ስሙ ይመስገን ምን ይባላል ሌላ
ያማረ እልልታ መቅደሱ ይሞላ
ይክበር ይመስገን ምን ይባላል ሌላ
ያማረ እልልታ መቅደሱ ይሞላ

2. የወግ ማእረግ አባት ሆኖ ስንቴ አየነው
እግዚአብሄር ይችላል ማክበር ልማዱ ነው
የድሃ ደግ አባት እርሱ ምን ይሳነው? /ወ/
ቀድሞ እርሱ ያየልን ቡቃያው ድረሰ
ጣፋጭ ሆነ ፍሬው ከሱ ለቀመሰ
እግዚአብሄር ይመስገን ደስታችንን ያደሰ /ሴ/

ስሙ ይመስገን ምን ይባላል ሌላ
ያማረ እልልታ መቅደሱ ይሞላ
ይክበር ይመስገን ምን ይባላል ሌላ
ያማረ እልልታ መቅደሱ ይሞላ

3. ስሙ አይነሳም ሰውን አሳፍሮ
እግዚአብሄር በስራው እንደ ኖረ ከብሮ
ያንንም ይኼንንም ሁሉንም አክብሮ /ሴ/
ምስክሮች አለን ቃል የምንሰጥለት
ሞገሳችን ሆኖ ይኼን ያየንበት
ደስታችን እርሱ ነው ዛሬ የምንልበት /ወ/

ስሙ ይመስገን ምን ይባላል ሌላ
ያማረ እልልታ መቅደሱ ይሞላ
ይክበር ይመስገን ምን ይባላል ሌላ
ያማረ እልልታ መቅደሱ ይሞላ /2/

ደስም አለን /4/

 

ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች
ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች
መንፈሴም በእርሱ ትደሰታለች
ጌታ የባሪያውን ውርደት አይቷል
ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል /2/

1. ብርቱ የሆነው በእኔ ታላቅ ስራ አድርጓል
ቅዱስ ስሙን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ አድርጓል
ለሚፈሩት ምህረቱ ለዘለአለም ይኖራል
እስከ ትውልድ ይተርፋል (ሴ)
ለሺ ትውልድ ይተርፋል (ወ)

ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች
መንፈሴም በእርሱ ትደሰታለች
ጌታ የባሪያውን ውርደት አይቷል
ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል

2. በሐያል ክንዱ ስራ ትእቢተኞችን ቀጥቶ
ሀሳባቸውን በትኗል ከዙፋኑ አዋርዶ
ትሁታንንም ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል
ማዳኑንም ይገልጻል (ሴ)
ማዳኑንም ያሳያል (ወ)

ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች
መንፈሴም በእርሱ ትደሰታለች
ጌታ የባሪያውን ውርደት አይቷል
ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል

3. በጎ ነገር አጥግቧል የተራቡትን
ባዱአቸውን ሰዷል ባለጸጎችን
ዘለአለም ምህረቱ ትዝ ይለዋልና
ጎበኘን እንደገና (ሴ)
አሰበን እንደገና (ወ)

ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች
መንፈሴም በእርሱ ትደሰታለች
ጌታ የባሪያውን ውርደት አይቷል
ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል

4. እርሱ የቅዱሳንን እግር ይጠብቃል
ደሀውን ምስኪኑን ከውድቀት ያነሳል
ዛሬም እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና
ይገባዋል ምስጋና (ሴ)
እንሰዋለት ምስጋና (ወ)

ክብር እንዴት ይነሳት
1. መልክተኛው እንኳን የእ/ር መላዕክት
በአክብሮት ተልኮ በክብር ቀረባት
ከሴቶች መካከል የተባረክሽ አላት
መንገዱ እኮ እርሷ ናት የጌታዬ ምፃት

ክብር እንዴት ይነሳት የመድሃኒቴ እናት
እንደርሷ ያለ ጠፍቶ ለብዙ ዘመናት
ምፃቱ ዘግይቶ ጊዜያት የረዘሙት
በእርሷ ተከናውኗል አርሷኮ ልዩ ናት

2. ሕዝቦች ቢመረጡም ነቢያት ቢላኩም
ከቶ መች ነበረ መልካም ለአምላኩ
ዝቅተኛይቱን እርሷን አገኘና
በጣሙን ፈለጋት ልቧንም አየና

ክብር እንዴት ይነሳት የመድሃኒቴ እናት
እንደርሷ ያለ ጠፍቶ ለብዙ ዘመናት
ምፃቱ ዘግይቶ ጊዜያት የረዘሙት
በእርሷ ተከናውኗል አርሷኮ ልዩ ናት

3. እምዬ ልዩ ናት የመድሓኒቴ እናት
የሱሴን ስትወልድ መች ቦታ ነበራት
መቼ እንደ እናቶች ወግ ደረሳትና
እንኳንስ መኖሪያ አልነበረም መና

ክብር እንዴት ይነሳት የመድሃኒቴ እናት
እንደርሷ ያለ ጠፍቶ ለብዙ ዘመናት
ምፃቱ ዘግይቶ ጊዜያት የረዘሙት
በእርሷ ተከናውኗል አርሷኮ ልዩ ናት

ብዙ ብዙ ነው
1. ወግ ማዕረግ አየሁ አንተን አግኝቼ
ሥቃዬን ረሳሁ ባይንህ ታይቼ
ውለታህን ታዲያ በምን ልግለፀው
ሚመጥንልኝ ቃላትን አጣሁ

ያረክልኝን ብቆጥረው ውለታህንም ሳስበው
የሰው አይምሮ አይገምተው እጅግ በጣም ብዙ ነው /2/
ብዙ ብዙ ነው አልችልም ልቆጥረው
ብዙ ብዙ ነው ከቁጥርም በላይ ነው
ብዙ ብዙ ነው አልችልም ልገምተው
ብዙ ብዙ ነው ከግምትም በላይ ነው

2. ፀጋህ እኮ ነው ዛሬን ያሳየኝ
አቅፎ ደግፎ ሰው ያደረገኝ
ምን ይገልፀዋል ያረከውን ለእኔ
የምልህ የለኝም ክበር መድህኔ

ያረክልኝን ብቆጥረው ውለታህንም ሳስበው
የሰው አይምሮ አይገምተው እጅግ በጣም ብዙ ነው /2/
ብዙ ብዙ ነው አልችልም ልቆጥረው
ብዙ ብዙ ነው ከቁጥርም በላይ ነው
ብዙ ብዙ ነው አልችልም ልገምተው
ብዙ ብዙ ነው ከግምትም በላይ ነው

3. በምድረ በዳ እጆቼን ይዘህ
ነፍሴን ከሚሿት ሁሉ ታድገህ
በመልካም መንገድ አንተው መራሃት
የሕይወትን ውሃ እያጠጣሃት

ያረክልኝን ብቆጥረው ውለታህንም ሳስበው
የሰው አይምሮ አይገምተው እጅግ በጣም ብዙ ነው /2/
ብዙ ብዙ ነው አልችልም ልቆጥረው
ብዙ ብዙ ነው ከቁጥርም በላይ ነው
ብዙ ብዙ ነው አልችልም ልገምተው
ብዙ ብዙ ነው ከግምትም በላይ ነው

ይኸው ተሰምቶልኝ ፀሎቴ
ይኸው ተሰምቶልኝ ፀሎቴ አምሮ ሰመረልኝ ምኞቴ
ይኸው እዘምራለሁ ለጌታ ላረገልኝ ብዙ ውለታ
ይኸው እዘምራለሁ ለጌታ ለዋለልኝ ብዙ ውለታ

1. ይመሰክራል ዛሬ አኗኗሬ
እንደረዳኸኝ የሱስ መድህኔ
አለኝ ምልክት ያንተ እርዳታ
ስኬቴ ሁሉ ባንተ ነው ጌታ /2/

ዝም አይልም ውለታህን አይቶ
ልቤ ያፈልቃል ምስጋናን ሞልቶ
ልዘምርልህ በአደባባይ
አምልኮን ላብዛ በላይ በላይ

ይኸው ተሰምቶልኝ ፀሎቴ አምሮ ሰመረልኝ ምኞቴ
ይኸው እዘምራለሁ ለጌታ ላረገልኝ ብዙ ውለታ
ይኸው እዘምራለሁ ለጌታ ለዋለልኝ ብዙ ውለታ

2. ከወደቅኩበት ከትቢያ አንስተህ
ሰው አደረከኝ እንዲህ ውብ አርገህ
ታዲያ ብዘምር ስላንተ ዝና
ሲያንስህ እንጂ መቼ በዛና /2/

አላቋርጥም ላንተ ምስጋና
እጨምራለሁ ገና አለኝ ገና
ከሆንከኝ አቅም ካለ እስትንፋሴ
ታመልክሃለች ሁል ጊዜ ነፍሴ

አላቋርጥም ላንተ ጭብጨባ
እጨምራለሁ መቅደስህ ይግባ
ከሆንከኝ አቅም ካለ እስትንፋሴ
ትወድሃለች ሁል ጊዜ ነፍሴ

ይኸው ተሰምቶልኝ ፀሎቴ አምሮ ሰመረልኝ ምኞቴ
ይኸው እዘምራለሁ ለጌታ ላረገልኝ ብዙ ውለታ
ይኸው እዘምራለሁ ለጌታ ለዋለልኝ ብዙ ውለታ

ክብር ዛሬም እንጨምር
ክብር /3/ ዛሬም እንጨምር
ምህረት ለምታስተምር
ሞገስ/3/ ለስምህ ይድረስ
አሜን ከፍ በል ንገስ

1. በዕድሜዬ ካለፍኩት ካወዳደርኩት
የሚበልጥ የለም ባንተ ካየሁት
አንድያ ልጁን ፈቅዶ እስኪስጠኝ
በፍፁም የለም ወዶ የወደደኝ
ተባረክ /2/ ተወደስ /2/
ባንተ ላይ ማንም አይደርስ /4/

2. ፍጥረት ምግባሩ ሆኖ የለመደው
አምልኮ አለህ ማንም የማይወደው
ከቶም ላይደክም ለእግዚአብሔር ብሎ
ሁሉም ያመልክሃል ሀይሉን ጠቅልሎ
ተባረክ /2/ ተወደስ /2/
ባንተ ላይ ማንም አይደርስ /4/

3. አንዱ ቀን አልፎ ሌላ ሲመጣ
ምስጋና ላንተ ተገኘም ታጣ
ለምህረትህ ልክ ለመውደድህ
ዛሬ ቀኑ ነው ለሚወድህ
ተባረክ /2/ ተወደስ /2/
ባንተ ላይ ማንም አይደርስ /4/

ክብር /3/ ዛሬም እንጨምር
ምህረት ለምታስተምር
ሞገስ/3/ ለስምህ ይድረስ
አሜን ከፍ በል ንገስ

 

ቸር እግዚአብሔር ሆይ
ቸር እግዚአብሔር ሆይ /2/
ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ
መልካም አይደለም እንዳልክ
ይህን ትዳር ባርክ
ይህንን ቤት ባርክ /2/

1. በማስተዋል እንዲጸና
በጥበብም እንዲቀና
በመረዳት ባለጸግነት
በሆድ ፍሬዎችም በረከት /2/

ቸር እግዚአብሔር ሆይ /2/
ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ
መልካም አይደለም እንዳልክ
ይህን ትዳር ባርክ
ይህንን ቤት ባርክ /2/

2. የቤታቸው መሰረቱ
አንተ ነህና ዓለቱ
የማይናወጥ ይሆናል
ተስማምተን አሜን ብለናል /2/

ቸር እግዚአብሔር ሆይ /2/
ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ
መልካም አይደለም እንዳልክ
ይህን ትዳር ባርክ
ይህንን ቤት ባርክ /2/

በአንድ ሃሳብ ተስማሙ
1. በከንቱ ዉዳሴ አንዳች አታድርጉ
ለራስ የሚሆንም ምንም አትፈልጉ
ለሌላ ማሰብን ይህንን እወቁ
ከሁሉም በፊት ግን በአንድ ሃሳብ ተስማሙ

በአንድ ሃሳብ ተስማሙ በአንድ ልብ ሆናችሁ
ፍቅርና ምሕረት እንዲበዛላችሁ /2/

2. በማያምኑት መሐል ቃሉን አክብራችሁ
በዓለም እንደብርሃን እየተያያችሁ
በምፅዓት ቀን ጌታ እንዲያስባችሁ
በአንድ ሃሳብ ተስማሙ በአንድ ልብ ሆናችሁ

በአንድ ሃሳብ ተስማሙ በአንድ ልብ ሆናችሁ
ፍቅርና ምሕረት እንዲበዛላችሁ

3. ምን ጊዜም በጌታ ደስታ ይሰማችሁ
ሀዘን ቅሬታንም ሁሉ አስወግዳችሁ
ቃሉን ማሰራጨት እንዴት ደስ ይላችሁ
በአንድ ሃሳብ ተስማሙ በአንድ ልብ ሆናችሁ

በአንድ ሃሳብ ተስማሙ በአንድ ልብ ሆናችሁ
ፍቅርና ምሕረት እንዲበዛላችሁ /2/

ያለው ይሆናል
እግዚአብሔር ያለው ይሆናል
ሰው መልከመልኩ ሁሌ ይዳክራል
የእርሱ ሃሳብ ሁሉ ይፈፀማል
የፈቀደው ይከናወናል

ያለው ይሆናል አሃ አሃ
ጌታ ያለው ይሆናል
ይከናወናል አሃ አሃ
እርሱ ካለ ይሆናል

1. እኔ ጉልበት አንዳችን ላልጨምርም
ከፀጉሬ እንኳን አንዷን ላልቀይርም
እንዲያው ስሮጥ ምንም ላይተርፈኝ
የሚያስገባኝን አገኘሁኝ

ይኸው ዛሬ ግን ጌታ ሲጐበኘኝ
ለጥያቄዬ ሁሉ መልስ አዘጋጀልኝ
እርሱ ባለው ቀን ጌታ ባቀደልኝ
ለእንቆቅልሼ ሁሉ መልስ አገኘሁኝ

ያለው ይሆናል አሃ አሃ
ጌታ ያለው ይሆናል
ይከናወናል አሃ አሃ
እርሱ ካለ ይሆናል /2/

2. ያለው ላይቀር ሲደርስ ሰዓቱ
በራስ ሃሳብ ላይ ታች ማለቱ
ላይሞላልኝ ጊዜን መፍጀቱ
የሚለፋት እንዲያው በከንቱ

ጌታ ባለው ቀን ፈቅዶ ሲወስን
ቀድሞ ያቀድኩት ሁሉ አየሁ ሲፈፀም
ምንም ቢዘገይም ለኔ ባይመስልም
ጌታ ያከናውናል በእርሱ አላፍርም

ሆኖ አይተናል አሃ አሃ
ጌታ አድርጐ አየተናል
ይከናወናል አሃ አሃ
ጌታ ካለ ይሆናል /2/

ያለው ይሆናል አሃ አሃ
ጌታ ያለው ይሆናል
ይከናወናል አሃ አሃ
እርሱ ካለ ይሆናል /2/

ገናና ነው
ገናናው/3/ ኢየሱስ ኃይለኛው /2/

1. የፍጥረታት ሁሉ ንጉሥ ነው
ማንስ እርሱን ሊስተካከለው
ሁሉን በፍቃዱ ያደርጋል
ጌታዬን ማን ያማክረዋል /2/

ገናናው/3/ ኢየሱስ ኃይለኛው /2/

2. ሲኦልን ድል የነሳ ጌታ
በኃይሉ ችሎት የበረታ
ዝናው በምድር ሁሉ የናኘ
እንደ ኢየሱስ ያልተገኘ /2/

አዳኝ ነው/3/ ፍቅር የሞላው/2/

3. ከዛ ከጨለማ ግዞት
የሞት ደምፅ ከሚሰማበት
አዳነኝ ኢየሱስ የኔ ጌታ
ድንቅ ነው ኸረ የሱስ ውለታ /2/

አዳኝ ነው/3/ ፍቅር የሞላው/2/

4 . በቁስሉ ቁስሌን የዳሰሰ
ደዌዬን ሁሉ የፈወሰ
ፍቱን መድኃኒት የዘላለም
ማንም እንደ ጌታዬ የለም /2/

ፈዋሽ ነው/3/ መድኃኒት ያለው

አይጥልም
1. በቆፈረው ጉድጓድ አሃ ጠላትን የሚጥል
አዋጅ በአዋጅ ሽሮ የሚሰጠን ድል
መከታ መመኪያ ታዳጊ አባት አለን
ድል የሚያጎናፅፍ ነጻ የሚያወጣን አሃ አሃሃ

አይጥልም አይተውም አይረሳም /2/
ይክበር የኔ ጌታ ይግነን የኔ ጌታ
ይንገስ የኔ ጌታ በማንም የማይረታ /2/

2. መካኒቷ ወልዳ አሃ ጸሎቷን ሰሞቶላት
ደስታ የሆነላት እንዲህ ያከበራት
እግዚአብሔር ታማኝ ነው ቃሉን የሚፈፅም
እርሱን የታመነ ፈፅሞ አይወድቅም ኧኸ ኧኸኸ

አይጥልም አይተውም አይረሳም /2/
ይክበር የኔ ጌታ ይግነን የኔ ጌታ
ይንገስ የኔ ጌታ በማንም የማይረታ /2/

3. ለነገስታት ድልን የሚያጎናፅፈው
ከስለታም ሰይፍ ደግሞ የሚታደገው
ቃልኪዳኑ ፅኑ እርሱ የታመነ ነው
ፍቅሩ የማይሻር ዘላለማዊ ነው ኧኸ ኧኸኸ

አይጥልም አይተውም አይረሳም /2/
ይክበር የኔ ጌታ ይግነን የኔ ጌታ
ይንገስ የኔ ጌታ በማንም የማይረታ /2/

እግዚአብሔር ብርቱ ነው
ፍጥረታት ሁሉም ያድንቀው
እግዚአብሔር ብርቱ ነው
ልመስክር ማዳኑን አየው  /2/

እግዚአብሔር ያለው (ሴ) ….. አይወድቅም ሰላም አለው
እግዚአብሔር ያለው (ሴ) ….. አይራብም ጸጋ አለው
እግዚአብሔር ያለው (ሴ) ….. ጨለማ አያስፈራው
እግዚአብሔር ያለው (ሴ) ….. አይሰጋም እምነት አለው /2/

አይጥልም አይተውም አይረሳም /2/
ይክበር የኔ ጌታ ይግነን የኔ ጌታ
ይንገስ የኔ ጌታ በማንም የማይረታ /2/

የበዓል

Leave a Comment

Scroll to Top