1. ለዚች ቀን ደርሰናል አንተን ተመርኩዘን
ሃጢያት እንዳይነካን ባንተ ሃይል ስር ሆነን
ለአንተ እንሰግዳለን ለታላቁ ስምህ
እዚህ ላደረስከን በሃያሉ ክንድህ /2/
በሃያሉ ክንድህ
ከክፉ ጠብቀህ
እዚህ ያደረስከን
ቅዱስ አምላካችን ተመስገን /2/
2. በሰጠኸን ሁሉ ጸንተን እንቆማለን
ጽድቅህን ለመውረስ ተስፋ እናደርጋለን
ዘውትር ልንወድስህ በፊትህ ቆመናል
ተቀብለን ልንኖር ዘላለም ያንተን ቃል /2/
ስለዚህ ጌታችን
ክብር ይገባሃል
ምስጋና ይገባሃል
ስግደት ይገባሃል አምልኮ /2/
3. ወንድሞች እህቶች ድምጻችንን እናንሳ
ያደረገልንን ምህረት እንዳንረሳ
ከማይደፈርሰው ቅዱስ ምንጭ አጠጣን
ፍጹም በሆነ ፍቅር በህይወት አቆየን
ቃሉን ተከትለን
ትዕዛዙን ፈጽመን
በመጨረሻው ቀን
ጌታችን ሲመጣ ህያው ነን /2/
