የኢየሱስ ልብ
የኢየሱስ ልብ የህይወቴ ነህ ጣዕም
አንተን ይውደድ ለዘላለም
ልቤ ላንተ ብቻ ሆኖ ይኑር
ላንተ ይሁን ዛሬና ዘወትር
1. የመጣሁት እመኻከላችሁ
ቅዱስ ፍቅርን ላነድላችሁ
ምኞቴንም ደግሞ ልንገራችሁ
ያመጣሁት ሲቃጠል ባየሁ
2. ባወቅክማ የፍቅሬን ስፋቱን
ልጄ ልቤን የሚያግለውን
በመጣህ ይዘህ ምስጋናህን
በደስታ ገንዘቤ ልትሆን
3. እንድወድህ አንተ ትሻለህ ወይ
እንድወድህ መጣህ ወይ ከላይ
ዋ ለኔማ ክብሬ አይደለህም ወይ
ፍጹም ንጉሥ የምድር የሰማይ
4. አንድ ምኞት ሌላም አልደባልቅ
ያንተን ፍቅር እንዳልነጠቅ
አንተን ከቶ ከቶም አለመራቅ
ብሞትም ብቆምም ብወድቅ
አሳ አጥማጅ ነበርኩኝ
ካንተ ተለይቼ ወዴት እሄዳለሁ
አንተ የሕይወት ቃል እንዳለህ አውቃለሁ /2/
1. አሳአጥማጅ ነበርኩኝ ለእለት ጉርስ የምኖር
ና ብለህ ስትጠራኝ የህይወት ቃል ልትሰጠኝ
ወደ ህይወቴ ገብተህ ኑሮዬን ለወጥከው
ሰዎችን እዳጠምድ አገልጋይ አረከኝ
ካንተ ተለይቼ ወዴት እሄዳለሁ
አንተ የሕይወት ቃል እንዳለህ አውቃለሁ /2/
2. መቅበዝበዜን አይተህ መውደቅ መነሳቴን
በአንተ አሳረፍከኝ አድሰህ ህይወቴን
እንዲህ ያለ እረፍት ማን ሊሰጥ ይችላል
እየሱስ ለኔ ግን አትረፍርፈኸዋል
ካንተ ተለይቼ ወዴት እሄዳለሁ
አንተ የሕይወት ቃል እንዳለህ አውቃለሁ /2/
3. የጨለመን ተስፋ ብሩህ ስታደርገው
የተሰበረን ልብ የሱስ ስትጠግነው
ነፍሴ ይህን አይታ ያላንተ ብላለች
ለህይወቷ እረኛ አንተን አድርጋለች
ካንተ ተለይቼ ወዴት እሄዳለሁ
አንተ የሕይወት ቃል እንዳለህ አውቃለሁ /2/
ሀሌ ሉያ
1. ሁሉን የምትገዛ በገናናው ክብርህ
እግዚአብሔር አምላክ ላንተ እንስገድልህ
በቃልህ ትዕዛዝ አለምን የፈጠርክ
ጉልበት ሁሉ ላንተ ለሥምህ ይንበርከክ
ሀሌ ሉያ /4//2X
2. ሁሉን ትረታለህ ኃይል አለ በክንድህ
ኦ! ጌታ ድንቅነህ ማነው የሚመስልህ
ቅዱስ ነህ እያልን እናመልክሀለን
በስልጣንህ እዘዝ ታላቅ ስምህ ይግነን
ሀሌ ሉያ /4//2X
3. አንተ ብቻ ጌታ አንተ ብቻ ንጉስ
አቻ አይገኝልህ ለዘላለም ቅዱስ
አንተ ስትገለጥ በክብር ስትቆም
ሊቃወም የሚችል አንድም ኃይል አይኖርም
ሀሌ ሉያ /4//2X
4. ማለዳ ማለዳ ያንተ ታማኝነት
አዲስ ነው ብዙ ነው ይገባሀል ስግደት
ዝማሬና እልልታ ይሙላው ጉባኤውን
በፅድቅ ተመላለሰ አክብረው ስምህን
ሀሌ ሉያ /4//2X
5. ከቶ ትዋሽ ዘንድ እንደ ሰው አይደለህ
ቃልህ የፀና ነው በምን እንመስልህ
ሥግደታችን ይኸው በመንፈስ በእውነት
ከዙፋንህ ይድረስ አንተው ክበርበት
ሀሌ ሉያ /4//2X
ቅዱስ ቁርባን
- በመንበርህ ቤተክርስቲያን፣
ከፍተህልን የህይወት መግቢያን፣
የደከመው ባንተ አርፏል፣
ገበታህም ፅዋው ተርፏል።
ያለ እየሱስ ለምትደክሙ፣
ላቆሰለው ሀጥያት ሸክሙ፣
እንኩ ያለን ሳይገባን፣
መድሀኒት ነው ቅዱስ ቁርባን።
አዝ:- እየሱስ እራሱን ሰጠን
በኛ ውስጥ ሊኖር መረጠን
ሲያከብረን ሲያሳየን ፍቅሩን
ሰቶናል ቁርባነ ሚስጥሩን
እየሱስ በቅዱስ ቁርባን
በኛ ውስጥ ሊኖር ተገባን
ክርስቶስ በቅዱስ ቁርባን
መንግስቱ ዳግም አገባን
ኢየሱስ ህይወትን ሰጠን /3/
ለመንግስቱ ዳግም አገባን
- ስጋውን ለኛ የቆረሰ
ክቡር ደሙ ነው የፈሰሰ
ለስጋም ለነብስም መድህን
እንቅረብ በፍርሀት አሁን /2/
አዝ:- እየሱስ እራሱን ሰጠን
በኛ ውስጥ ሊኖር መረጠን
ሲያከብረን ሲያሳየን ፍቅሩን
ሰቶናል ቁርባነ ሚስጥሩን
እየሱስ በቅዱስ ቁርባን
በኛ ውስጥ ሊኖር ተገባን
ክርስቶስ በቅዱስ ቁርባን
መንግስቱ ዳግም አገባን
ኢየሱስ ህይወትን ሰጠን /3/
ለመንግስቱ ዳግም አገባን
- ክቡር ደሙን ለኛ አፍስሶ፣
ከአካሉ ስጋውን ቆርሶ፣
ታላቅ ሚስጥር አካፈለን፣
የዘላለም ህይወት ሲለን።
መንገዱ ነው የመዳኑ፣
አሜን ብለው ለታመኑ።
በንስሀ መንገድ ፅኑ፣
ወደ ሚስጥረ ቁርባን ኑ።
አዝ:- እየሱስ እራሱን ሰጠን
በኛ ውስጥ ሊኖር መረጠን
ሲያከብረን ሲያሳየን ፍቅሩን
ሰቶናል ቁርባነ ሚስጥሩን
እየሱስ በቅዱስ ቁርባን
በኛ ውስጥ ሊኖር ተገባን
ክርስቶስ በቅዱስ ቁርባን
መንግስቱ ዳግም አገባን
ኢየሱስ ህይወትን ሰጠን /3/
ለመንግስቱ ዳግም አገባን
ውለታህ ብዙ
አዝ. ውለታህ ብዙ አንተ የሰራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔ ስላንተ ውለታ /2/
1. ስንቱ ተወርቶ ስንቱ ይተዋል ጌታ ሆይ
ለእኔ ያረከው ቀና ብዬ አንተን ሳይ
ከጭንቀት አውጥተህ ሰላም የሰጠኸኝ አባት ሆይ
ክብርና ምስጋና ላንተ ይሁን የሱስ ሆይ
አዝ. ውለታህ ብዙ አንተ የሰራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔ ስላንተ ውለታ /2/
2. መሬት በሙሉ ወደ ወረቀት ቢለወጥ
ባህር በሙሉ ወደ ቀለምም ቢቀየር
ያረከው ጌታ ቢታይ የአንተ ውለታ
በፍጹም አልችልም ቃላት ያጥረኛል ጌታ
አዝ. ውለታህ ብዙ አንተ የሰራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔ ስላንተ ውለታ /2/
3. ቢጻፍ አያልቅም ጌታ የአንተ ውለታ
ስራህ ድንቅ ነው ከቶ የማትረታ
የእስራኤል አምላክ ከቶ የማታንቀላፋ
የእስራኤል አምላክ ከቶ የማታንቀላፋ
አዝ. ውለታህ ብዙ አንተ የሰራዊት ጌታ
ምንስ ልክፈልህ እኔ ስላንተ ውለታ /2/
ገናና ነው
ገናናው/3/ ኢየሱስ ኃይለኛው /2/
1. የፍጥረታት ሁሉ ንጉሥ ነው
ማንስ እርሱን ሊስተካከለው
ሁሉን በፍቃዱ ያደርጋል
ጌታዬን ማን ያማክረዋል /2/
ገናናው/3/ ኢየሱስ ኃይለኛው /2/
2. ሲኦልን ድል የነሳ ጌታ
በኃይሉ ችሎት የበረታ
ዝናው በምድር ሁሉ የናኘ
እንደ ኢየሱስ ያልተገኘ /2/
አዳኝ ነው/3/ ፍቅር የሞላው/2/
3. ከዛ ከጨለማ ግዞት
የሞት ደምፅ ከሚሰማበት
አዳነኝ ኢየሱስ የኔ ጌታ
ድንቅ ነው ኸረ የሱስ ውለታ /2/
አዳኝ ነው/3/ ፍቅር የሞላው/2/
4 . በቁስሉ ቁስሌን የዳሰሰ
ደዌዬን ሁሉ የፈወሰ
ፍቱን መድኃኒት የዘላለም
ማንም እንደ ጌታዬ የለም /2/
ፈዋሽ ነው/3/ መድኃኒት ያለው
አይጥልም
- በቆፈረው ጉድጓድ አሃ ጠላትን የሚጥል
አዋጅ በአዋጅ ሽሮ የሚሰጠን ድል
መከታ መመኪያ ታዳጊ አባት አለን
ድል የሚያጎናፅፍ ነጻ የሚያወጣን አሃ አሃሃ
አይጥልም አይተውም አይረሳም /2/
ይክበር የኔ ጌታ ይግነን የኔ ጌታ
ይንገስ የኔ ጌታ በማንም የማይረታ /2/
2. መካኒቷ ወልዳ አሃ ጸሎቷን ሰሞቶላት
ደስታ የሆነላት እንዲህ ያከበራት
እግዚአብሔር ታማኝ ነው ቃሉን የሚፈፅም
እርሱን የታመነ ፈፅሞ አይወድቅም ኧኸ ኧኸኸ
አይጥልም አይተውም አይረሳም /2/
ይክበር የኔ ጌታ ይግነን የኔ ጌታ
ይንገስ የኔ ጌታ በማንም የማይረታ /2/
3. ለነገስታት ድልን የሚያጎናፅፈው
ከስለታም ሰይፍ ደግሞ የሚታደገው
ቃልኪዳኑ ፅኑ እርሱ የታመነ ነው
ፍቅሩ የማይሻር ዘላለማዊ ነው ኧኸ ኧኸኸ
አይጥልም አይተውም አይረሳም /2/
ይክበር የኔ ጌታ ይግነን የኔ ጌታ
ይንገስ የኔ ጌታ በማንም የማይረታ /2/
እግዚአብሔር ብርቱ ነው
ፍጥረታት ሁሉም ያድንቀው
እግዚአብሔር ብርቱ ነው
ልመስክር ማዳኑን አየው /2/
እግዚአብሔር ያለው
አይወድቅም ሰላም አለው
እግዚአብሔር ያለው
አይራብም ጸጋ አለው
እግዚአብሔር ያለው
ጨለማ አያስፈራው
እግዚአብሔር ያለው
አይሰጋም እምነት አለው
እግዚአብሔር ያለው
አይወድቅም ሰላም አለው
እግዚአብሔር ያለው
አይራብም ጸጋ አለው
እግዚአብሔር ያለው
ጨለማ አያስፈራው
እግዚአብሔር ያለው
አይሰጋም እምነት አለው
አይጥልም አይተውም አይረሳም /2/
ይክበር የኔ ጌታ ይግነን የኔ ጌታ
ይንገስ የኔ ጌታ በማንም የማይረታ /2/
ለእኔ ያደላል
እግዚአብሔር ያደረገው በእኔ ላይ ተአምር
ብዙ እኮ ነው ሰዎች ስሙኝ ልናገር /2/
ከአፈር ላይ አንስቶ እንዲህ ልዘምር
ኧረ እንዴት ወደደኝ ጌታ እግዚአብሔር /2/
ለእኔ /5/ ያደላል ለኔስ ያደላል /2/
ለኔስ /2/ አደላ ለኔስ አደላ /2/
የሆነልኝ አለ አዲስ /2/ ነገር
እግዚአብሔር ካዘዘኝ ይህን እንድናገር
ለኔ እማኝ እኔው ነኝ ለኔ እርሱ ልዩ ነው
ያየሁትን ሁሉ እመሰክራለሁ
የሆነልኝ አለ አዲስ /2/ ነገር
እግዚአብሔር ካዘዘኝ ይህን እንድናገር
ለኔ እማኝ እኔው ነኝ የእግዚአብሔር ህዝብ ይኸው
በሰውነቴ ላይ ያረገውን እየው
አልተለየኝም (ወ) …ስንቱን ሳጣው ፊቴ(ሴ)
አልተለየኝም(ወ)…ደርሶልኛል ስንቴ(ሴ)
አልተለየኝም(ወ)…ከኔ ለምዶ ሌላ(ሴ)
አልተለየኝም(ወ)…አላለኝም ችላ(ሴ)
አልተለየኝም…ጉድ አደባባይ
አልተለየኝም..መኃል መንገዱ ላይ
አልተለየኝም…አሳለፈኝ ማዶ
አልተለየኝም…እንዴት ይጥላኝ ወዶ
ለእኔ /5/ ያደላል ለኔስ ያደላል /2/
ለኔስ /2/ አደላ ለኔስ አደላ /2/
ኧረ እንዴት
1. አስቤ እሮጬ ማልዘልቀው
እቅዴን ኢየሱስ አሳመረው
ባምላኬ ጣፍጦልኝ ኑሮዬ 2x
ለምልሞ አየሁት ተስፋዬ
ኧረ እንዴት /2/ ልርሳዉ
ውለታው ውስጤን ከበደዉ
አልቻልኩም እንደው ዝም ማለት
ተነሳሁ ልመሰክርለት
2. ያለፍኩት ያን ሁሉ በህይወቴ
በእርሱ ነው ኢየሱስ እረዳቴ
ዛሬ እንዴት አስችሎኝ ልለፈው 2x
ውለታው ኧረ እንደምን ልርሳው
ኧረ እንዴት /2/ ልርሳዉ
ውለታው ውስጤን ከበደዉ
አልቻልኩም እንደው ዝም ማለት
ተነሳሁ ልመሰክርለት
3. ጠላቴ ሲመኝልኝ ሞቴን
ጌታ ነው የተቤዣት ነፍሴን
እንደ ህልም ሁሉም አለፈና 2x
ለወጠው ታሪኬን እንደገና
ህይወቴ ያማረው በእርሱ ነው /2/
ነገሬ ያማረው በእርሱ ነው /2/
ጌታን ተደግሬ ያለፍኩትን ዘመን
ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው
በእኔ አቅም ብርታት
ይታለፋል ማለት ዘበት ነው
ጌታ ሆኖልኝ አቅም ብርታቴ
ዛሬን አየሁት አምሮ ሀይወቴ
